ከ«ሃዳኒሽ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''ሀዳኒሽ''' በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ የሐማዚ ንጉሥ ሲሆን ከኪሽ ነገሥታት በኋላና ከ[[ኡ...»
(No difference)

እትም በ15:18, 20 ማርች 2011

ሀዳኒሽሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ የሐማዚ ንጉሥ ሲሆን ከኪሽ ነገሥታት በኋላና ከኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና በፊት በሱመር ላዕላይነቱን ለ360 አመታት ያዘ። እንዲህ ረጅም ያለ ጊዜ እንደ ነገሠ ባይታስብም እንኳን ለጥቂት ዘመናት (ምናልባት 2240-2210 ዓኮልበ. አካባቢ) በአገሩ እንደ ቆየ በቃላል ይቻላል። በሌላ ምንጮች በኩል ስሙ የሚገኝ በአንድ ሰነድ ብቻ አለ። ከብዙ መቶ ዘመን በኋላ የተጻፈ በኒፑር መቅደስ የነበሩት የባቢሎን ጣኦታት ዝርዝር እንደሚለው፣ በመቅደሱ በር ጎን ለጎን 2 የስፊንክስ ጣኦታት ስሞች «ሃታኒሽ እና ሉማ» ተባሉ። «ሉማ» ማለት የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ሌላ (አሞራዊ) ስም ነው፤ ደግሞ ሀዳኒሽ በኒፑርና ኪሽ እየገዛ ኤአናቱም በላጋሽ እንደ ነገሠ ይቻላል። የነገሥታት ዝርዝር ኤንሻኩሻና ከሀዳኒሽ የሱመር ላይኛነት እንደ ያዘ ሲል ኤንሻኩሻና እራሱ የኤአናቱም ተወዳዳሪ ሆነ።