ከ«ካልቡም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ካልቡም''' በ[[ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር]] ላይ የ[[ኪሽ]] 2ኛው ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበረ። የማማጋል (መርከበኛው) ልጅ ሆኖ ዘመኑ ለ195 አመታት እንደ ቆየ ሲል ይህ ግን ትክክለኛ አይመስልም። ከ[[የአዋን ሥርወ መንግሥት|አዋን (ኤላም) ነገሥታት]] ቀጥሎ ኪሽ ላዕላይነቱን እንደ ያዘ ይለናል። በኪሽ የነገሡ ንጉሦች 1) ሱሱዳ የሱፍ ጠራጊ፣ 2) ዳዳሲግ፣ 3) ማማጋል መርከበኛው፣ 4) ካልቡም የማማጋል ልጅ፣ 5) ቱጌ፣ 6) መን-ኑና የቱጌ ልጅ፣ 7)...(?) 8) ሉጋል-ጙ ናቸው ይለናል። ዳሩ ግን ለነዚህ ነገሥታት ሁሉ አንዳችም ሌላ ቅርስ ገና አልተገኘም። መጀመርያ 3 ስሞች የካልቡም ቅድመ-አባቶች ይሆናሉ፣ እንጂ ንጉሳዊ ስሞች አይመስሉም። ኪሽ በዚህ ወቅት ላዕላይነቱን ከያዘ ቅርስ ባለመገኘቱ ዘመኑ አጭር መሆን አለበት። ከካልቡም በኋላ የተዘረዘሩ ስሞች በሱመር ላዕላይ ነገሥታት ሳይሆኑ ምናልባት የከተማው ከንቲቦች ብቻ ነበሩ። ከኪሽ በኋላ የ[[ሐማዚ]] ንጉሥ [[ሃዳኒሽ]] እንደ ተነሣ ዝርዝሩ ይጨምራል።
 
ከኪሽ 2ኛ ሥርወ መንግሥት ሁሉ የ1 ንጉሥ ስም ምናባትምናልባት በቅርስ ሊትይ ይችላል። በ[[1962]] ዓ.ም. ሊቁ [[ቶርኪልድ ያቆብሰን]] እንደ መሰለው፣ በ[[ላጋሽ]] ንጉሥ [[ኤአናቱም]] ጽላት ላይ የኪሽ ንጉሥ በኤአናቱም ጦር ጫፍ ላይ ሲያሳይ ጽሕፈቱ ምናልባት «የኪሽ ንጉሥ ካልቡም» ይላል።<ref>Thorkild Jacobsen, ''Toward the image of Tammuz and other essays on Mesopotamian history and culture'' 1970, p. 393.</ref>
 
<references/>