ከ«ግስበት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.6.4) (ሎሌ መጨመር: be:Гравітацыя
Robot-assisted disambiguation: ሜርኩሪ - Changed link(s) to ኣጣርድ
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Solar sys.jpg|right|350px|thumb| [[ፕላኔት|ፈለኮች]] በ[[ምህዋር|ምህዋራቸው]] ከ[[ፀሐይ]] አምልጠው እንዳይሄዱ የሚያስገድዳቸው የግስበት [[ጉልበት]] ነው ]]
 
'''ግስበት''' ማናቸውም [[ግዝፈት]] ያላቸው ቁስ ነገሮች እርስ በርሳቸው እንዲሳሳቡ ግድ የሚላቸው የተፈጥሮ [[ጉልበት]] ነው። በዕለት ተለት ኑሯችን ግዝፈት ያላቸው ነገሮች በአየር ከመንሳፈፍ ይልቅ ከመሬት ጋር እንዲላተሙ የሚያደረጋቸው፣ በሌላ አነጋገር ለነገሮች [[ክብደት]] የሚሰጣቸው ግስበት ነው። የመሬት ግስበት ወይም በተለምዶ የ[[መሬት ስበት]] መሬት ባላት ግዝፈት ምክንያት ሌላ ግዝፈት ያለውን ነገር የምትስብበት የተፈጥሮ ጉልበቷ ነው። [[ጨረቃ]] ከመሬት በራ የማትጠፋው የመሬት ግስበት አንቆ ስለያዛት ነው። [[ኣጣርድ|ሜርኩሪ]]ን፣ [[ቬነስ]]ን፣ ሌሎች የተቀሩትን [[ፕላኔት|ፈለኮችን]] በ[[ፀሐይ]] ዙሪያ ጠፍሮ ከ[[ምህዋር|ምህዋራቸው]] በረው እንዳይጠፉ የሚያደርጋቸው የፀሐይ ግስበት ነው። [[ኮከብ|ከዋክብት]]ንና ሌሎች ግዙፍ ቁሶችን በየ[[ረጨት|ረጨታቸው]] መድቦ አስተቃቅፎ የሚይዛቸው ይኽው መሰረታዊ ጉልበት ነው። ግስበት፣ ባጠቃላይ መልኩ ፣ በጥልቁ [[ጠፈር]] ውስጥ ተበትኖ የሚገኘውን ቁስ እንዲጓጉል ያደርጋል። ከዚህ አንጻር ለመሬት፣ ለተስፈንጣሪ ከዋክብት፣ ለ [[ፕላኔት|ፈለኮች]] (ፕላኔቶች) ፣ ለ[[ኮከብ|ከዋክብት]]፣ ለ[[ረጨት|ረጨቶችና]] መሰል ግዙፍ አካላት ጓጉሎ መፈጠርና ቀጣይ ህልውና ይህ ጉልበት አስፈላጊና በርግጥም መሰረታዊ ነው ፤ አለበለዚያ የመጓጎልና አንድ ሁነው የመቀጠል እድል አይገጥማቸውም ነበርና። በውቅያኖሶች ለሚፈጠሩ [[ማዕበል|ማዕበሎች]]፣ ለ[[ወንዝ|ወንዞች]] መፍሰስ፣ ለአዳዲስ ከዋክብትና ፈለኮች ውስጣው ከፍተኛ ሙቀት እና ሌሎች ህልቁ መሳፍርት ክስተቶች ተጠያቂ ጉልበት ነው።
 
== የግስበት ጥናት ታሪክ ==
መስመር፡ 18፦
 
==== የኒውተን ህግ ወሰኖች ====
ከኒውተን መነሳት 200 አመት በኋላ፣ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በተደረጉ ጥንቃቄ የተሞላባቸው ክትትሎች የ[[ኣጣርድ|ሜርኩሪ]] ምህዋር በጣም ጥቃቅን መርበትበት እንደሚያሳይ ታወቀ። ይህን መርበትበት በኒውተን ህግጋት ለመግለጽ ተሞክሮ ሳይሳካ ቀረ። ይህ ችግር በንዲህ ሁኔታ ሳይፈታ ቆይቶ [[አልበርት አይንስታይን]] በ1915 አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህን ፕላኔት የምህዋር መርበትበት በአዲሱ [[አጠቃላይ አንጻራዊነት]] ብሎ በሰየመው መጽሃፉ በአጥጋቢ ሁኔታ ጉዳዩን ሊፈታው ቻለ።
በአሁኑ ዘመን በርግጥ የኒውተን ህግ በ[[አይንስታይን]] የ[[አጠቃላይ አንጻራዊነት]] ህግጋት ቢሻሻልም፣ አብዛኛው ዘመናዊ የግስበት ስሌት እስካሁን ድረስ የሚሰራው የኒውተንን ርዕዮት በመጠቀም ነው። ምክንይቱም የኒውተን ህግ
* ቀላል ስለሆነ