ከ«ጌባል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: ከነዓን - Changed link(s) to ከነዓን (ጥንታዊ አገር)
መስመር፡ 1፦
'''ጌባል''' ([[አረብኛ]]፦ جبيل /ጁባይል/፤ [[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪክ]]፦ Βύβλος /ቢውብሎስ/) በ[[ሊባኖስ]] የሚገኝ ጥንታዊ ከተማ ነው።
 
የጥንቱ [[ፊንቄ]] ታሪክ ጸሐፊ [[ሳንኩኒያቶን]] እንዳለ፣ ጌባል ከሁሉ ጥንታዊ ከተማ ሲሆን በንጉሡ [[ክሮኖስ]] (ወይም 'ኤሎስ') በፊንቄ ([[ከነዓን (ጥንታዊ አገር)|ከነዓን]]) አገር ተመሠርቶ ነበር። ለረጅም ጊዜ ከተማው የ[[ምስር]] [[ፈርዖን]] ጓደኛ ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በ[[መዝሙረ ዳዊት]] 83፡7 እና [[ትንቢተ ሕዝቅኤል]] 27፡9 ይጠቀሳል። በኋላ (747 ዓክልበ.) ጌባል ለ[[አሦር]] ንጉሥ [[3 ቴልጌልቴልፌልሶር]] ተገዥ ሆነ። እንዲሁም በየተራው ወደ [[ፋርስ]]፣ [[መቄዶን]] እና [[ሮማ]] መንግሥታት ተዛወረ፤ ከዚያም ለአረቦች ወደቀ። በ[[መጀመርያው መስቀል ጦርነት]] ([[1092]] ዓ.ም) ስሙ 'ጊብለት' ተብሎ ለጊዜ የፈረንጆች ማዕከል ሆነ። ከ[[1508]] እስከ [[1911]] ዓ.ም. በ[[ኦቶማን]] (ቱርክ) መንግሥት ነበር። ከተማው እስከ ዛሬ ድረስ በሊባኖስ ይገኛል።
 
በጥንት ጌባል [[ፓፒሩስ]] (የ[[ወረቀት]] ተክል) ወደ ግሪኮች የነገደው ዋናው ወደብ ስለ ሆነ፣ ግሪኮች የከተማውን ስም Βύβλος /ቢውብሎስ/ አሉት፤ ይህም በግሪክ ቋንቋ 'ፓፒሩስ' ወይም 'መጽሐፍ' ማለት ነበር። ይህ ቃል በ[[እንግሊዝኛ]] የ«Bible» (/ባይብል/፣ መጽሐፍ ቅዱስ) ምንጭ ሆነ።