ከ«ትርኪ ተራራ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
robot Modifying: en:Turkey Mountain (Oklahoma)
Robot-assisted disambiguation: ከነዓን - Changed link(s) to ከነዓን (ጥንታዊ አገር)
መስመር፡ 1፦
'''ትርኪ ተራራ''' በ[[ቱልሳ]] አካባቢ [[ኦክላሆማ]] ክፍላገር [[አሜሪካ]] ውስጥ ከ[[አርካንሳው ወንዝ]] አጠገብ የሚገኝ ሲሆን እንዲያውም ተራራ ሳይሆን ትልቅ ኮረብታ ነው። በዚያ ላይ በተገኙት ድንጋዮች ላይ ያሉት ምልክቶች 'የጥንታዊ አሜሪካ መዝገቦች' ተብለዋል። በአንድ ዋሻ ውስጥ የተቀረጹት ስዕሎችና ምልክቶች ከውቅያኖስ ማዶ የመጡት መርከበኞች ሥራ መሆናቸውን አንዳንድ ምሁር ያምናል።
 
በዋሻው የሚታይ አንዱ ምልክት [[የላቲን አልፋቤት]] ፊደላት «PIA» ይመስላል። ከዚህ በላይ አንዳንድ መስመር ሊታይ ይችላል። አወዛጋቢው ምሁር [[ባሪ ፌል]] ይህን «PIA» የሚለውን ቃል ከ«A»-ኡ ቅርጽ የተነሣ እጅግ ጥንታዊ መሆኑን ገመተ። በሱ አስተሳሰብ በ[[ከነዓን (ጥንታዊ አገር)|ከነዓን]] ቋንቋ የተጻፈው 'ፓያ' ወይም 'ነጭ' ለማለት ነው። መስመሮቹ ደግሞ የ[[ኦጋም]] ፊደል መስለውት በ[[ጎይደሊክ]] ቋንቋ 'ጒን' ወይም 'ነጭ' እንደሚል ያምናል። በሁለት ቋንቋዎች የተጻፈ ቃል ማለቱ ይሆናል።
 
ይህ ሥፍራ ልክ በ[[ጋዲር]] ('የሄራክሌስ ዓምዶች' ወይም የዛሬው [[ካዲዝ]]) [[ኬክሮስ]] ላይ (36 N) ይገኛል። በ[[መጽሐፈ ኩፋሌ]] መሠረት ከጋዲር ወደ ምዕራብ የሚሄድ መስመር የ[[ሞሳሕ]] [[ያፌት]] ርስት ከከነዓን [[ካም]] ርስት ይለያል።