ከ«ዐምደ ጽዮን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 25፦
 
== የአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመንና ዘመቻዎች ==
=== ዘመቻ ወደ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ኢትዮጵያ ===
ዐምደ ጽዮን በእንዴት መንገድ ወደ ስልጣን እንደመጡ መረጃ የለም፣ ስለሆነም ታሪክ አጥኝው [[ታደሰ ታምራት]] ንጉሱ ከአባታቸው ጋር ትግል ገጥመው ዘውድ ላይ እንደወጡ መላ ምት ያቀርባል <ref>ታደሰ ታምራት፣ pices 4, ቅጽ 1, ገጽ 505</ref> ። ንጉሱ በመንግስታቸው መጀመሪያ (፲፫፻፲፮ ዓ.ም. ) የተሳካላቸው ዘመቻዎች በ[[ጎጃም]]፣ [[ዳሞት]]ና [[ሐድያ]] በማድረግ እኒህ አካባቢወች እንዲገብሩ ሆነ<ref>Marrasini, Lo Scettro e lacroce, La Camagna Di 'Amda Seyon I contro l'Ifat (1332)</ref>። ሆኖም በኒህ ዘመቻወች ትኩረታቸው ስለተሳበ በተገኘው ክፍተት የ[[እንደርታ]] ገዢ የነበረው [[ይብቃ እግዚ]] የ[[አምባ ሰናይት]]፣ [[ብልሃት]]ንና [[ተምቤን]] ሰራዊትን በማደራጀት በንጉሱ ላይ ተነሳ <ref> ታደሰ ታምራት፣ 1970፣ ገጽ 95f</ref>። በ1320ዓ.ም ንጉሱ የይብቃ እግዚን አመጽ ከደመሰሱ በኋላ በ[[አምባ ሰናይት]] የጦር ዕዝ አቋቋመው ወደ ስሜን በመዝመት እስከ [[ቀይ ባህር]] ድረስ ያለውን ክፍል ለመቆጣጠር ቻሉ <ref>ታደሰ ታምራት 1970: ገጽ 95</ref>። በዚህ ወቅት እንደረታን እንድታስተዳድር የተሰየመችው የ[[ትግሬ]] ተወላጅ የነበረችው የንጉሱ ሚስት ንግስት [[ብሌን ሳባ]] ነበረች። ስልጣኗም [[ባልታ ብሃት]] በመባል ይታወቅ ነበር። ቆይቶ እንደርታን እንዲያስተዳድር የተደረገው የንጉሱ ሦሥተኛ ልጅ [[ባህር አሰገድ]] በ[[ማዕከለ ባህር]] ማረግ ነበር፣ ግዛቱም እስከ ቀይ ባህር ወደብ ድረስ የተንሰራፋ ነበር <ref>Conti Rossini, 1901: ገጽ 34</ref>።
 
=== ዘመቻ ወደ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ===
የንጉሱ ትኩረት ወደ ሰሜን መሆኑን የተረዱት የደቡብ እስላማዊ ክፍሎች፣ በቀይ ባህር ንግድ ላይ ያላቸውን ቁጥጥር እና ሃይል ተመርኩዘው የአርብቶ አደሩን ክፍል በማስተባበር የሃይል ማደግ አሳዩ። በተለይ በ[[ወላስማ]] ሱልጣኖች የሚመራውና በደቡብ ምዕራብ [[ሸዋ]] የሚገኘው የ[[ይፋት]] ግዛት በሃይል ተጠናከረ። ይህ ክፍል፣ ከአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመን በፊት ጀምሮ ለመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ግብር ከፋይ ነበር። ሆኖም ክፍሉ በዚህ ዘመን እራሱን ችሎ ለመገንጠል ፈለገ <ref>ታደሰ ታምራት፣ ቤተከርስቲያንና ሀገር፣ ገጽ 130</ref>። በዚህ ሁኔታ የክርስቲያንና የእስልምና ግዛት በሰሜንና በደቡብ እየተጠናከሩ ሁለት የሃይል ማዕከሎች በመፍጠር ፉክክር ውስጥ ገብተው ከፍተኛ ጦርነት መነሳቱ ግድ ሆነ።
 
ወደ [[ግብጽ]] ተልኮ የነበረው [[ጥንታይ]] የተሰኘው የንጉሡ መልዕክተኛ [[ሃቀዲን]] በተባለ የይፋት ገዢ መታሰር በመጨረሻ ጦርነቱ ገንፍሎ እንዲወጣ አደረገ። ዐምደ ጽዮን ይፋትን ከደመሰሰ በኋል በ[[ጀበል]]ና [[ወርጂ]] አርብቶ አደሮች ተቃጥቶበት የነበረውን ጥቃት ድል በማድረግ እንዲሁም የክርስቲያን ክፍሎች፣ [[ተጉለት]]፣ [[ዝጋ]] ና [[መንዝ]] አመጾችን በማጥፋት ሃቃዲንን በማሰር ከስልጣን አስወገደው ። በርሱ ቦታ ወንድሙን [[ሳባራዲን]]ን ከላይ የተገለጹት ክፍሎችን አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመው።