ከ«ዐምደ ጽዮን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot: Replacing category የኢትዮጵያ ታሪክ with የኢትዮጵያ ነገሥታት
No edit summary
መስመር፡ 1፦
ቀዳማዊ '''አጼ ዐምደ፡ጽዮን''' (የዙፋን ስም '''ገብረ መስቀል''') ከ[[1314]] እስከ [[1344]] ዓ.ም. የነገሡ ሲሆን በጥንቱ ዘመን ከተነሱ ነገሥታት ውስጥ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሰፋ ያለ አሻራ ትተው ካለፉት (ለምሳሌ፦ [[ዘርአ ያዕቆብ]] ) ጎን ወይም በላይ ስማቸው ይጠቀሳል<ref>Edward Ullendorff, his review of Huntingford's translation of ''The Glorious Victories of Amda Ṣeyon, King of Ethiopia'', [http://www.jstor.org/stable/611476 ''Bulletin of the School of Oriental and African Studies, University of London''], 29 (1966), p. 600</ref> ። አጼ ዐምደ ጽዮን የአጼ [[ይኩኖ አምላክ]] የልጅ ልጅና የአጼ [[ወድም አራድ]] ልጅ እንደሆኑ ይታመናል<ref>Basset I, II</ref>፡፡ ይኩኖ አምላክ አዲሱን የ[[ሰሎሞን ስርወ መንግስት]] ቢመሰርቱም፣ በልጅ ልጆቻቸው የነበረው ፉክክርና አዲስ ከሚስፋፋው የ[[እስልምና]] ሃይማኖት የሚሰነዘረው ጥቃት ስርዓቱን ስጋት ላይ የጣለ ነበር። አጼ አምደ ጽዮን ይህን ፉክክር በማስቆምና በዘመናት በማይደበዝዘው ጀግንነታቸው የኢትዮጵያን ድንበር ከሞላ ጎደል አሁን በሚታወቀው መልኩ በማስቀመጥ፣ የአዲሱን ስርወ መንግስት መሰረት በማጽናት እንዲሁም በማረጋጋት ዝናቸው በጥንቱ አለም ክ[[አፍሪቃ ቀንድ]] እስከ [[አውሮጳ]] የተንሰራፋ ነበር <ref>Cerulli 1932</ref>።
'''አጼ አምደ፡ጽዮን''' (የዙፋን ስም '''ገብረ መስቀል''') ከ[[1314]] እስከ [[1344]] ዓ.ም. የነገሱ ሲሆን የ[[ደብረ ሊባኖስ]]ን ገዳም ያስሩት እኒሁ ንጉስ ነበሩ። ስምንቱ የደቡብ መንግስታትም፣ የ[[ሱማሌ]]ንና የ[[ሃድያ]]ን ጨምሮ ለሱ ግብር ይከፍሉ እንደነበር [[ሳልት]] የተሰኘው የእንግሊዝ ጻህፊ ዘግቦት ይገኛል። የኢትዮጵያም ደበር በ[[ኢየሩሳሌም ]] የተከፈተው በኒሁ ንጉስ መልካም ፈቃድ ነበር። ከዚህ በተረፈ «የወታደሩ እንጉርጉሮ» የተሰኙት አራቱ የ[[አማርኛ]] መዛግብት በዚህ ዘመን እንደተጻፉ ታሪክ ዘጋቢወች ይናገራሉ።
 
== የአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመንና ዘመቻዎች ==
ዐምደ ጽዮን በእንዴት መንገድ ወደ ስልጣን እንደመጡ መረጃ የለም፣ ስለሆነም ታሪክ አጥኝው [[ታደሰ ታምራት]] ንጉሱ ከአባታቸው ጋር ትግል ገጥመው ዘውድ ላይ እንደወጡ መላ ምት ያቀርባል <ref>ታደሰ ታምራት፣ pices 4, ቅጽ 1, ገጽ 505</ref> ። ንጉሱ በመንግስታቸው መጀመሪያ (፲፫፻፲፮ ዓ.ም. ) የተሳካላቸው ዘመቻዎች በ[[ጎጃም]]፣ [[ዳሞት]]ና [[ሐድያ]] በማድረግ እኒህ አካባቢወች እንዲገብሩ ሆነ<ref>Marrasini, Lo Scettro e lacroce, La Camagna Di 'Amda Seyon I contro l'Ifat (1332)</ref>። ሆኖም በኒህ ዘመቻወች ትኩረታቸው ስለተሳበ በተገኘው ክፍተት የ[[እንደርታ]] ገዢ የነበረው [[ይብቃ እግዚ]] የ[[አምባ ሰናይት]]፣ [[ብልሃት]]ንና [[ተምቤን]] ሰራዊትን በማደራጀት በንጉሱ ላይ ተነሳ <ref> ታደሰ ታምራት፣ 1970፣ ገጽ 95f</ref>። በ1320ዓ.ም ንጉሱ የይብቃ እግዚን አመጽ ከደመሰሱ በኋላ በ[[አምባ ሰናይት]] የጦር ዕዝ አቋቋመው ወደ ስሜን በመዝመት እስከ [[ቀይ ባህር]] ድረስ ያለውን ክፍል ለመቆጣጠር ቻሉ <ref>ታደሰ ታምራት 1970: ገጽ 95</ref>። በዚህ ወቅት እንደረታን እንድታስተዳድር የተሰየመችው የ[[ትግሬ]] ተወላጅ የነበረችው የንጉሱ ሚስት ንግስት [[ብሌን ሳባ]] ነበረች። ስልጣኗም [[ባልታ ብሃት]] በመባል ይታወቅ ነበር። ቆይቶ እንደርታን እንዲያስተዳድር የተደረገው የንጉሱ ሦሥተኛ ልጅ [[ባህር አሰገድ]] በ[[ማዕከለ ባህር]] ማረግ ነበር፣ ግዛቱም እስከ ቀይ ባህር ወደብ ድረስ የተንሰራፋ ነበር <ref>Conti Rossini, 1901: ገጽ 34</ref>።
 
 
'''አጼ አምደ፡ጽዮን''' (የዙፋን ስም '''ገብረ መስቀል''') ከ[[1314]] እስከ [[1344]] ዓ.ም. የነገሱ ሲሆን የ[[ደብረ ሊባኖስ]]ን ገዳም ያስሩት እኒሁ ንጉስ ነበሩ። ስምንቱ የደቡብ መንግስታትም፣ የ[[ሱማሌ]]ንና የ[[ሃድያ]]ን ጨምሮ ለሱ ግብር ይከፍሉ እንደነበር [[ሳልት]] የተሰኘው የእንግሊዝ ጻህፊ ዘግቦት ይገኛል። የኢትዮጵያም ደበር በ[[ኢየሩሳሌም ]] የተከፈተው በኒሁ ንጉስ መልካም ፈቃድ ነበር። ከዚህ በተረፈ «የወታደሩ እንጉርጉሮ» የተሰኙት አራቱ የ[[አማርኛ]] መዛግብት በዚህ ዘመን እንደተጻፉ ታሪክ ዘጋቢወች ይናገራሉ።
 
{{መዋቅር}}