ከ«መስ-አኔ-ፓዳ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''መስ-አኔ-ፓዳ''' በ[[ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር]] ላይ የ[[ኡር]] መጀመርያው ንጉሥ ነበረ። በዚያው ዝርዝር ዘንድ የ[[ኡሩክ]]ን ንጉሥ ሉጋል-ኪቱንን አገልብጦ ለ80 ዓመታት ነገሠ። ከ[[ሥነ ቅርስ]] በዕውኑ እንደ ነገሠ እርግጥኛ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለ ረጅም ዘመን እንደ ገዛ ግን አጠያያዊ ነው።
 
እስከዚህ ድረስ፣ ለ[[ሱመር]] ላዕላይነት ዋና ተዋዳዳሪዎች ኡሩክና [[ኪሽ]] ነበሩ። [[ጊልጋመሽ]] የኪሽን ንጉሥ [[አጋ]]ን አሸንፎ [[ኒፑር]]ንም ከተማ ይዞ ላዕላይነቱን ለኡሩክ መሠርቶ ነበር። አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀየረ፤ የኡርም ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ተነሥቶ ኡሩክን፣ ኪሽን፣ ኒፑርንና መላ ሱመርን ያዘ። ከዚያ በኋላ «የኪሽ ንጉስ» የሚለው ማዕረግ ወሰደ።
መስመር፡ 5፦
''ቱማል ጽሑፍ'' በተባለው ጽላት፣ ከጊልጋመሽ ልጅ [[ኡር-ኑንጋል]] ቀጥሎ መስ-አኔ-ፓዳ የኒፑርን ዋና መቅደስ ጠባቂ ነበረ።
 
መስ-አኔ-ፓዳ ለ[[ማሪ]] ንጉሥ (በ[[ሶርያ]]) ስጦታ እንደ ላከ ከ[[ሥነከሥነ ቅርስ]] ይታወቃል፤ አንድ ዶቃ እዚያ ተገኝቶ በጽሕፈቱ መስ-አኔ-ፓዳ የ[[መስካላምዱግ]] ልጅ ይባላል። እንዲሁም በኡር በንጉሣዊ መቅብሮች የመስ-አኔፓዳና ቀዳሚዎቹ የመስካላምዱግ፣ የ[[አካላምዱግ]]ና የንግሥት [[ፑአቢ]] ስሞች ሁሉ ተመዘገቡ።
 
ከመስ-አቤ-ፓዳ በኋላ ልጁ [[መስኪአጝ-ኑና]] እንደተከተለው በማለት ''የነገሥታት ዝርዝር''ና ''የቱማል ጽሑፍ'' ይስማማሉ። ሌላ የመስ-አኔ-ፓዳ ልጅ [[አ-አኔ-ፓዳ]] ቤተ መቅደስ በኡር አካባቢ እንዳሠራ ይታወቃል።