ከ«ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ስመ ሞክሽ የነበሩት ብላታ ወልደጊዮርጊስን የሚመለከተው ዘገባ ከዚህ ተወገደ።
(ስመ ሞክሽ የነበሩት ብላታ ወልደጊዮርጊስን የሚመለከተው ዘገባ ከዚህ ተወገደ።)
የስድሳ ስድስቱ አብዮት ኃይለ ሥላሴን ከሥልጣን ከማውርዱ ከጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ ለሕክምና ወደ እንግሊዝ አገር ይሄዱና ሁለተኛውንና የመጨረሻውን የስደት ዘመን ጀምረው በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው እዚያው እንግሊዝ አገር አርፈው ተቀበሩ።
 
==ሥነ ጽሑፍ==
[[ስዕል:Qdusge maryam.JPG|thumb|right|ቅዱስጌ ማርያም ቤ/ክርስቲያን - ቡልጋ]]
[[ስዕል:Qdusge Maryam2.JPG|thumb|right]]
 
የተባሉፀሐፊ ይገኙባቸዋል።ትዕዛዝ ከዚህም ሌላወልደጊዮርጊስ በተወለዱበት [[ቡልጋ]] ውስጥ የቅድስጌ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን በግል አሠርተዋል።
ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር በመሆን መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከ[[ግዕዝ]] ወደ [[አማርኛ]] ተርጉመዋል፡፡ በ[[1914|፲፱፻፲፬]] ዓ/ም [[ቤተ ሳይዳ]] ይባል የነበረው ጋዜጣ ሲቋቋም ምክትል አዘጋጅ በመሆን፣ ብርሃንና ሰላም]] ጋዜጣና [[ከሣቴ ብርሃን]] ለልብ ጠቢባን ይባል የነበረው መጽሔት ዝግጅት አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ በኋላም የ[[ሰንደቅ ዓላማችን]]ና የ[[አዲስ ዘመን]] ጋዜጣን በኃላፊነት፣ በዲሬክተርነትና በረዳት ሚኒስትርነት እንዲሁም የማስታወቂያ ሚኒስቴር አማካሪ በመሆን ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል፡፡
 
እኝህ ታላቅ ጋዜጠኛና የሥነ ጽሑፍ ሰው አሥራ ሰባት ያህል መጻሕፍትንና እንዲሁም የተለያዩ መጣጥፎችን አዘጋጅተዋል፡፡ ከሥራዎቻቸውም ውስጥ ''አግአዚ'' የተሰኘው ልብወለድ መጽሐፋቸው ይጠቀሳል፡፡ ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ለአማርኛ ቋንቋ ካበረከቷቸው ሌሎች ድርሰቶች
 
1. የወንድ ልጅ ኩራት ስለሀገር መሞት
2. የዓለም ጠባይ ሐሴትና ብካይ
3. ከሥራ በኋላ ሥራ ስትፈቱ እንቆቅልሽ ተጫወቱ
4. ሥነምግባር
5. አምስት መንገደኞች
 
የተባሉ ይገኙባቸዋል። ከዚህም ሌላ በተወለዱበት [[ቡልጋ]] ውስጥ የቅድስጌ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን በግል አሠርተዋል።
 
== ከድርሰቶቻቸው ==
 
===ከአምስት መንገደኞች ([[1954|፲፱፻፶፬]] ዓ/ም)===
 
የሰው አሳብና የውሻ ጅራት ዘወትር ወደ ላይ ነው፡፡ ነገር ግን ውሻ በትር ሲመዘዝበት ጅራቱን እንዲሸጉብ፤ ሰውም ላይ ላዩን እላለሁ ሲል አንድ ዓይነት አደጋ ሲወድቅበት ጭብጥ እንኳ አይሞላም፤ ከአዳም መወለዱን የሚያምን ሁሉ ይህን ሊክድ አይችልም፡፡
 
ሰው ሃይማኖት ካለው በመከራም ላይ ቢወድቅ መከራም ቢወድቅበት ዘወትር በላይ ከመሆን በቀር በምንም አይጨነቅም፡፡ ስለዚህ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የሚባለው መንፈሳዊ ሊቅ በዘጠነኛው ድርሳኑ አንተ ሰው በዓይኖችህ ፊት የሃይማኖት መጠኗን አትናቅ፤ ናቂ የሆነ ዓይን በሃይማኖት ላይ ሊገለጽ አይቻልም፤ አባ፣ አባ ብታውቁባት ጐንደርም ዋልድባ ናት፤ እንደሚባለው ሰው ቢያውቅበት ሳይንስም ሃይማኖት አለበት፡፡
 
ሰውየው፤ ሰውየውን ውሻህን በቀበሮ ለውጠኝ ቢለው የሚያደምጠውን ትቼ የሚያለምጠውን የምለውጠው ምኔ ሞኝ ነው? አለው ይባላል፡፡ ሰው ዐዋቂ ከሆነ ዘንድ በሃይማኖት ረገድ አለዐዋቂ ይሆን ዘንድ ምኑ ሞኝ ነው? በሳይንስ ምርመራ ያገኘው ጥበብ በጣም ከፍ እያለ ሲሔድ በእግዚአብሔር ላይም ያለው እምነት በበለጠ አኳኋን ከፍ ከፍ ማለት አለበት፡፡
 
ስለዚህ በሳይንስ ረገድም የሚደረገው አስተያየት ለመልክአ ሃይማኖት የጠራ መስተዋት ሳይሆነው አለመቅረቱ የታወቀ ነው፡፡
 
ዱሮ አንድ ተማሪ መንገድ ሲሔድ ያገኙት ሰዎች ወዴት ትሔዳለህ? ቢሉት፣ ለትምህርት ወደ ዘጌ እሔዳለሁ፤ በስቲያውም ቡና ለቀማ አለ ይባላል፤ የሳይንስም ምርመራ እንዲሁ ነው፡፡ ሥጋዊ ጥበብን እንመረምራለን ሲባል፣ መንፈሳዊውም አብሮ ይገኛል፡፡
 
===ሁሉም ከመሬት ተፈጥሮአል===
 
ማንጠልጠያ የሌለው ከበሮ ከተጋደመበት ሲጐስሙት ድምፁን ማሰማቱ አይቀርም፡፡ ሃይማኖት የሌለው ሰው ግን ምን ድምፅ አለው፡፡"" ቢኖረውስ ምን ፍሬ ነገር ሊያሰማበት ነው ቢሆንም ከሃይማኖተ ውጭ አፍ እላፊ አላደርግም፡፡ "ሽንብራ ዱቤ አይገኝም በዱቤ" እንደ ተባለው የሃይማኖት ፍሬ ያለሃይማኖት በዱቤ ያለመገኘቱ እየታወቀ እንዴት ሰው ያለ ሃይማኖት ይኖራል፡፡ ይህማ እንደ እንስሶች መሆን አይደለምን፤ እንዳያውም እንስሳት ሃይማኖት ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም ምን ቸገራቸው፡፡ ቢጠመዱም፤ ቢታረዱም፤ ቢገረፉም፤ ቢገፊፉም፤ ጣጣቸው የሚያልቀው በዚሁ በታችኛው ዓለም ስለሆነ ከሞት በኋላ ነፃ ናቸው፡፡
 
ከዚህም ላይ ልብ የሚመታና በስሜት ላይ መገረምን የሚጥል ቃል በማግኘቴ ሲከነክነኝ ይኖራል፡፡ እሱ እኮ ነገረኛ ነው፡፡ ተጠራጥሮ ያጠራጥራል፡፡ "የሰው ልጆችና የእንስሳ እጣ ነው፡፡ ድርሻቸውም የተስተካከለ ነው፡፡ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከንቱ ነውና፡፡ ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሔዳል፡፡ ሁሉም ከመሬት ተፈጥሮአል፡፡ ሁሉም ወደ መሬት ይመለሳል፡፡ የሰው ልጆች ነፍስ ወደ ላይ እንድትወጣ፤ የእንስሳም ነፍስ ወደ ምድር በታች እንድትወርድ ለይቶ የሚያውቅ ማነው" ይላል፡፡
 
==አባባሎች==
* ደስ መሰኘትና መከፋት ሲዘዋወሩ ስለሚኖሩ ደስ ያለው እንደሚከፋው፣ የከፋው ደስ እንደሚለው አይጠረጠርም፡፡
* በዕድሜ መሰንበትና ፈተናን ሁሉ አልፎ ወደ ደህና ቀን መድረስ ብዙ ጊዜ መታደልና መክበር ነው፡፡
* በእናት ማኅፀን የተፀነሰ ፅንስ ቀኑ ሲደርስ በማኅፀን ታግዶ እንደማይቀር ሥራም በትጋት ከተጀመረ የሠራተኛው አሳብ ከወሰነው ጊዜ አያልፍም፡፡
* ፍልስፍና አድራሻ የለውም፤ ያለ ዕረፍት ሲሄድ የሚኖር የምርመራ አሞራ ከመሆኑም የተነሳ ከሁሉ ይደርሳል፡፡
* ማወቅ ወጣም ወረደ ለመደነቅ ብቻ አይደለም፤ ስህተት የሌለበት ሙሉ ሰውን ለመሆንም ነው እንጂ፡፡
* ሥጋ በመንፈስ እየተንቀሳቀሰ፣ መንፈስ በሥጋ እየተዳበሰ ግዙፍነትንና ረቂቅነትን ለመግለጽ፣ መንፈስ ወደ መንፈሳዊነት፣ ሥጋም ወደ ሥጋዊነት እያዘነበለ፣ በአንድ ሰው አካል ሁለት ኃይል ሲሠራ ይኖራል፡፡
(ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ 1935)
 
==ማጣቀሻ==
3,107

edits