ከ«መንዝ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 20፦
 
==ታሪክና ባህል ==
መንዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተጠቅሶ የሚገኘው በቀዳማዊ አጼ [[አምደ ጽዮን]] ዜና መዋዕል ሲሆን በጊዜው '''መንዝሔል''' ይባል ነበር <ref>G.W.B. Huntingford, ''The Historical Geography of Ethiopia'' (London: The British Academy, 1989), p. 80</ref>። ቀጥሎም በአጼ [[በእደ ማርያም]] ዜና መዋዕል ተጠቅሶ ይገኛል <ref>[[ስዕል:ChronicleofZeraYaqobAndBaedeMaryam.pdf| 100px|thumb| left| [[የአጼ በእደማርያምበእደ ማርያም ዜና መዋዕል]]፣ ገጽ 201 |page=201]] </ref> ።
 
መንዝ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ የያዘው በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጠናቀቂያ፣ በ[[ነጋሲ ክርስቶስ]] ነበር። የመንዝ ተወላጁ ነጋሲ የ[[አጋንጫ ኪዳነ ምህረት]]ን ቤተክርስቲያን በመመሰረት ሲታወቅ የ[[ፍሩክታ]]ንም ደብር በማስፋፋት ይጠቀሳል። ነጋሲ [[ታላቁ እያሱ]]ን ለመጠየቅ በሄደበት በትክትክ በሽታ ሲያርፍ ልጁ [[ሰባስቲያኖስ]] ሸዋን ከመንዝ ሆኖ ያስተዳድር ነበር። ኋላ ላይ የተነሱት [[ንጉስ አብይ]]፣ ምንም እንኳ እናታቸው ከ[[ላሎ ምድር]] የመጣች ብትሆንም መስተዳድራቸውን ከመንዝ ወደ [[ሐር አምባ]] በማዛወራቸው የመንዝ ማዕከላዊነት ደበዘዘ። የሆኖ ሆኖ መንዝ ለሚቀጥሉት ዘመናት ታዋቂ መሪወችን በማፍራትና በማስተናገድ ትታወቃለች። ለምሳሌ የነጋሲ ዘር የሆነው [[መርድ አዝማች አስፋ ወሰን]] በ18ኛው ክ.ዘመን መጨረሻ ጠላቶቹ ሲያሳድዱት በ[[ፍሩክታ ኪዳነ ምህረት]] እንደተጠለለ ይነገራል። የ[[ሳህለ ስላሴ]] እናት ወይዘሮ [[ዘነበወርቅ]]፣ የነጋሲ ዘር ሲሆኑ ዋና ከተማቸውን በ[[ሰላ ድንጋይ]]፣ [[ላሎ ምድር]] መስርተው ይኖሩ ነበር። እንዲሁም [[አቶ በዛብህ]] ("አባ ደቅር") የመንዝ ባላባት ሲሆኑ በ[[አጼ ቴዎድሮስ]] የአበጋዝ ሹም የነበሩና የአጠቃላይ ሸዋ አስተዳዳሪና ኋላ ላይ ከወደፊቱ [[አጼ ምኒልክ]] ሠራዊት ጋር በ[[አምባ ዳየር]] ጦርነት አድርገው የተሸነፉ ናቸው። ቆይቶም አጼ ምንሊክ በአምባ አፍቃራ፣ መንዝ፣ ቤተ መንግስትና የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ገንብተዋል። በኋላ በጣሊያን ወረራ ወቅት ለነበረው ትግል መንዝ ማዕከላዊ ሚናን ተጫውቷል።