ከ«መንዝ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 41፦
*[[አፍቀራ ስላሴ]] -- በ[[አቡነ ተክለሃይማኖት]] ዘመን የተቋቋመ. በምባ አፍቀራ ላይ የሚገኝ።
*[[ይልማ ገዳም]] -- በሰሜን ምዕራብ የመንዝ ጠረፍ የሚገኝ ሲሆን የባለ እጅ ገዳም በመባል ይታወቃል። በዚህ ገዳም፣ ወንዶችም ሆነ ሴቶች፣ የሸክላ ስራወችን ያመርታሉ ስለሆነም የ[[ባለ እጆች ገዳም]] ይባላል።
*[[አርበራ መድሃኔ አለም]] -- ከዋሻ አለት የተሰራና የተለያየዩ አጽዋማት የሚገኙበት ገዳም
 
== [[ጓሳ ሜዳ]] ==
የጓሳ ሜዳ በመንዝ የሚገኝ፣ወደ 110 ኪሎ ሜተር ስኩየር የሚጠጋ ስፋት ያለው፣ ከኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ ትልቁ የ[[አፍሮ አልፓይን]] ስርዓተ ህይወት ቅሪት ነው። በዚህ ሜዳ 26 ምንጮች ሲኖሩ ቦታው ሳይታረስ ለ400 አመታት የተለያዩ ብርቅ እንስሳት (ምሳሌ፡- [[ጭላዳ ዝንጀሮ]] (200 የሚጠጉ) ፣ [[ቀይ ቀበሮ]] (ከ20 እስከ 50 ብቻ የሚደርሱ) ፣ [[አጋዘን]]፣ ወዘተ...) መኖሪያ በመሆን አገልግሏል። የአካባቢው ህዝብ የዚህን ጉዳይ መሰረት ሲያስረዱ፣ ከላይ የተጠቀሰው ጻዲቁ ዮሐንስ ምስራቃዊ በዚህ አካባቢ ሲኖር ሳለ አንዲት ሴት በውሸት አስረግዞኛል ብላ ከሰሰችው። የአካባቢውም ህዝብ ይህን ክስ ከጻዲቁ ፊት እንድትደግም አደረጓት እርሷ ግን ክሱን መድገም ብቻ አይደለም "ከዋሸሁ ድንጋይ ያድርገኝ" ብላም ጨመረች። በዚህ መሰረት ንግግሯን ሳታቋርጥ ወደ ድንጋይ ተቀየረች። ጻዲቁም በማዘን ሜዳው ምንም እህል እንዳያበቅል ተራገመ። በዚህ መሰረት በጥሩ ጤፍ ምርቱ ይታወቅ የነበረው ጓሳ የተለያዩ አውሬዎች መኖሪያ ሆነ።
 
በአሁኑ ወቅት በጓሳ ሜዳ 7 ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ አጥቢ እንስሳት ይገኛሉ - ይህም ከአጠቃላዩ ኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙት አጥቢ እንስሳት 22.6% ነው። 111 የወፍ አይነቶች በመንዝ ሲገኙ ሰባቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ናቸው።
 
== ማጣቀሻ ==