ከ«ጊልጋመሽ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ጊልጋመሽ''' (ወይም '''ቢልጋመሽ'''፥ በቅድመኞቹ [[ሱመርኛ]] ጽላቶች) የ[[ኡሩክ]] 4ኛው ንጉሥ ነበረ። በ[[ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር]] ላይ 126 ዓመታት እንደ ነገሠ ይጠቀሳል። እንዲሁም ''[[የጊልጋመሽ ትውፊት]]'' የሚባለው ሥነ ጽሑፍ አለ። በዚህ በኩል አባቱ [[ሉጋልባንዳ]] ይባላል። ጊልጋመሽም በኡሩክ የነገሰው ከሉጋልባንዳ ተከታይ ከ[[ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ]] ቀጥሎ እንደ ነበር ይባላል።
 
በአንዱ ጽላት የ[[ኤንመባራገሲ]] ልጅ የ[[ኪሽ]] ንጉስ [[አጋ]] ከጊልጋመሽ ጋር ሲዋጋው፣ ጊልጋመሽ ያሸንፈዋል። ኤንመባራገሲና አጋ ታሪካዊ የኪሽ ነገሥታት መሆናቸው በስነ ቅርስ ረገድ እርግጠኛ ስለ ሆነ፤ ጊልጋመሽ ደግሞ አፈታሪካዊ ብቻ ሳይቀር ታሪካዊ ንጉስ እንደ ሆነ ይገመታል።