ከ«ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 58፦
እንግዲህ ባንድ በኩል ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ከንጉሠ ነገሥቱ በዐዋጅ በተሰጣቸው ሙሉ ሥልጣን ብዙ የሚፈሯቸውና የተከፉ መሳፍንት፣ መኳንንትና ባለሥልጣናት እንደጠሏቸውና የሳቸውን ከሥልጣን መውረድ በጉጉት ይጠባበቁ እንደነበር ተመልክተናል።
 
ቀጥሎም የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ (ማለትም ለንጉሠ ነገሥቱ ቅርብነትና ተሰሚነትን እያገኙ የመጡት) እንዲሁም የ’እንግሊዝ ደጋፊ’ ይባሉ የነበሩት ፀሐፌ ትዕዛዝ አካለተፈራ ወርቅ ኪዳነ ወልድ ከወልደ ጊዮርጊስ ጋር ያደርጉትን ሙግት ተመልክተን ምናልባት የጽሕፈት ሚኒስቴሩ ዘላቂና ኃይለኛ ባላጋራ አጋጥሟቸው ይሆን ለማለት እንችላለን።
 
በሦስተና ደረጃ የኤርትራን የኅብረት መንግሥት በተመለከት የንጉሠ ነገሥቱ ተግሳጽ በሌሎች (ተቃዋሚዎቻቸው) ፊት ሲደርሳቸው ጆን ማርካኪስ “በ[[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]] የአስተዳደር ስልት፤ ለሥልጣን የብቃተ ቢስነት ወንጀል ወይም የማይካድ የሙስና ድርጊት ሲታይ የተለመደው ቅጣት ወደሌላ ሥራ መዛወር ሲሆን፤ ለንጉሠ ነገሥቱ ታማኝ አለመሆን ግን ያለምንም ጥርጣሬ በፈጣን ፍርድ በግዞት ዓለም መጥፋትን ያስከትላል።” ያለን በፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስውጊዮርጊስ ላይ እየተተገበረ መሆኑን እንገነዘባለን።
 
ወዲያውኑ ፀሐፌ ትዕዛዝ ከጽሕፈት ሚኒስቴርነታቸው ተሽረው መጀመሪያ የ[[አርሲ|አሩሲ]] ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ ሆነው እስከ [[1953|፲፱፻፶፫]] ዓ/ም ከቆዩ በኋላ ወደ [[ጋሞጐፋ ዞን|ገሙ ጎፋ]] ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳድሪ ሆነው ተዛወሩ።
 
የስድሳ ስድስቱ አብዮት ኃይለ ሥላሴን ከሥልጣን ከማውርደኡከማውርዱ ከጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ ለሕክምና ወደ እንግሊዝ አገር ይሄዱና ሁለተኛውንና የመጨረሻውን የስደት ዘመን ጀምረው በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው እዚያው እንግሊዝ አገር አርፈው ተቀበሩ።
 
==ሥነ ጽሑፍ==