ከ«በለስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ መጨመር: te:ఫైకస్
ሎሌ መጨመር: az:Əncir; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[Fileስዕል:Sycomoros old.jpg|thumb|270px|የሾላ ዛፍ]]
'''በለስ''' ([[ሮማይስጥ]]፦ ''Ficus'') ቅጠሉ ሰፋፊ፣ ነጭ ፈሳሽ ያለው፣ ፍሬው የሚበላ የእፅዋት ዝርያ ነው። ፍሬውም ደግሞ በለስ ወይም ዕጸ በለስ ይባላል።
 
በበለሱ ቤተሠብ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የዛፍ አይነቶች አሉ፤ እነዚህም፦
 
* ተራ በለስ ''F. carica'' ከጥንት ጀምሮ ስለ ፍሬው በእርሻ ወይም በጓሮ ተተክሏል። ፍሬውም ለጤንነት እጅግ መልካም ነው።
* [[የቆላ በለስ]] ''F. palmata''
* [[ሾላ]] ''F sycomorus'' -
* [[ዋርካ (ዛፍ)|ዋርካ]] (ወይም ወርካ) ''F. vasta'' - በብዙ ቅርንጫፎች በጣም ትልቅ የሆነ የበለስ አይነት ነው። ፍሬው ከሾላ ፍሬ ያንሳል። ይህ ፍሬ ከበሰለና ከደረቀ በኋላ ይበላል።
* [[ባኒያን]] ''F. benghalensis''
* [[ችባሓ]] ''F. thonningii''
መስመር፡ 13፦
* [[የቊልቋል በለስ]] (''Opuntia'') እውነተኛ በለስ ሳይሆን እንዲያውም ቊልቋል ነው። ሆኖም ፍሬውን ስለሚመስል ብዙ ጊዜ ይህም ተክል 'በለስ' ይባላል።
 
የበለስ 'ፍሬ' በዕውኑ ወደ ውስጥ ያበበ [[አበባ]] ነው። ይህ ክስተት ለ[[ሥነ ሕይወት]] ጥናት በጣም የሚያስገርም ድንቅ ነው። እነኚህ አበቦች [[ፅጌ ብናኝ]]ን (የአበባ ወንዴ ዘር) የሚያገኙበት ዘዴ በልዩ ብናኝ አርካቢ ጥቃቅን [[ተርብ]] አማካኝነት ነው። ይህች [[የበለስ ተርብ]] ወደ ፍሬው ውስጥ ገብታ በመኖር እንቁላሏን በዚያ ትጥላለች። አብዛኞቹ በለስ አይነቶች አለበለዚያ ብናኝ ዘርን ሊያገኙ አይችሉም። ተርቢቱ ዕንቁላሏን ጥላ በበለሱ ውስጥ ከሞተች በኋላ፣ በፍሬው ያለው [[ኤንዛይም]] በድኑን ፈጽሞ ይበላል። የዛፉ ጾታ አንስት ከሆነ፣ የተርቢቱ እንቁላል አይፈለፈለም፣ ፍሬውም በሰው ይበላል። የዛፉ ጾታ ግን ፍናፍንት ሲሆን፣ ዕንቁላሎቿ ይፈለፈላሉ፤ ፍሬው ለፍየል ሊሰጥ ይችላል እንጂ በሰዎች አይበላም። ተርቦች ከፍናፍንት ዛፍ ተወልደው ሴት ተርቦቹ የሴት ዛፍ እንዲያገኙ ገበሬው የፍናፍንት ዛፍ ቅጠል ከአንስት ዛፍ ቅርንጫፍ ይሰቅላል። አንዳንድ የበለስ አይነት ያለ ተርብ ያፈራል፤ ነገር ግን የነዚህ ፍሬዎች መካን ይሆናሉ። ዳሩ ግን በለሶች በ[[እፃዊ ተዋልዶ]] ለማብዛት በተለይ ስለሚመቹ፣ ይህ ዘዴ የተለመደና ፈጣን የመራቦ ዘዴ ነው።
 
በ[[እስልምና]]፣ በ[[ሕንዱ]]፣ በ[[ቡድሂስት]]ና በ[[ጃይን]] እምነቶች፣ በለሶች የተቀደሱ ዛፎች ሆነው ይቆጠራሉ። በ[[ክርስትና]]ም በ[[አይሁድ]]ም በኩል በለስ ወይም ሾላ በ[[ብሉይ ኪዳን]] ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ለምሳሌ በአንዳንድ ሥፍራ በትንቢት፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ሰው ሁሉ በራሱ [[ወይን]]ና በለስ ሥር እንደሚቀመጥ ይላል። በተጨማሪ በ[[ኦሪት ዘፍጥረት]] 3፡7 ዘንድ [[አዳም]]ና [[ሕይዋን]] ከበለስ ቅጠል ልብስ ሠሩላቸው። ከዚህ የተነሣ በተለይ በ[[ኢኦተቤ|ተዋሕዶ ቤ.ክ.]] የበለስ ፍሬ ወይም እፀ-በለስ እግዚአብሔር እንዳትበሉት ብሎ ያዘዛቸው ፍሬ መሆኑን በመገመት ይታመናል። ሆኖም በሌላ አስተሳስብ የተከለከለው ፍሬ መታወቂያ ወይኑ ወይም [[ቱፋህ]] ነበር። መታወቂያው በመጽሐፉ እርግጠኛ ስላልሆነ፣ በእርግጥ በለስ ማለቱ ነበር ልንል አንችልም። በ[[አዲስ ኪዳን]] ውስጥ ደግሞ በለስ በ[[ኢየሱስ|ክርስቶስ]] ምሳሌዎች ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል፤ በ[[ማርቆስ ወንጌል]] ምዕራፍ 11 መሠረት ኢየሱስም አንዲቱን በለስ ረግሞ ነበር።
 
<gallery>
መስመር፡ 27፦
[[መደብ:ፍራፍሬ]]
 
[[az:Əncir]]
[[ca:Ficus]]
[[cs:Fíkovník]]