ከ«ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦
በሱመር [[አፈ ታሪክ]] ስለ ኡሩክ ንጉሥ ዱሙዚድ ዘመን የሚያወሩ በርካታ ሰነዶች ተገኝተዋል። በነዚህ ጽላቶች ውስጥ ግን የቅጽል ስሙ «አሣ አጥማጁ» ሳይሆን፣ የኡሩክ ንጉሥ ስም «[[ዱሙዚድ እረኛው]]» ይባላል። ነገር ግን በነገሥታት ዝርዝር ላይ፣ ሁለት ልዩ ልዩ ነገሥታት «[[ዱሙዚድ]]» ተብለዋል፤ እነርሱም ከ[[ማየ አይኅ]] በፊት በ[[ባድ-ቲቢራ]] የነገሠው «እረኛው» እና ከማየ አይኅ በኋላ በኡሩክ የነገሠው «አሣ አጥማጁ» ናቸው። ታሪኩ በነገሥታት ዝርዝሩ ላይ ትንሽ እንደ ተደባለቀ ይመስላል።
 
ጽላቶቹ እንደሚሉት፣ ይህ የኡሩክ ንጉሥ ዱሙዚድ በቅንጦት እየተቀመጠ፣ ድሆችና ረኅብተኞች ሰዎች (ወይም «ከይሲዎች» እንደሚባሉ) በአመጽ ተነሡበት። እንዳይዟት፣ ቁባት ባለሥልጣኗ [[ኢናና]] በርሷ ፋንታ ዱሙዚድን በመክዳት ወደ እጃቸው ሠጠችውና ሤረኞቹ ከዚያ ገደሉት።<ref>[http://etcsl.orinst.ox.ac.uk/cgi-bin/etcsl.cgi?text=c.1.4*# የዱሙዚድ ተረቶች፣ በእንግሊዝኛ ትርጉምና በኦሪጂናል ሱመርኛ]</ref> የሚከተለውየሚከተለውም የኡሩክ ንጉሥ ጊልጋመሽ ሲሆን በነገሥታት ዝርዝር ላይ ጊልጋመሽ «አባቱ ከይሢ የሆነ» ይባላል።
 
በኋለኛ [[አረመኔ]] እምነት፣ ዱሙዚድ እንደ ጣኦቱ [[ተሙዝ (ጣኦት)|ተሙዝ]]፣ ቁባቱም ኢናና እንደ ሴት ጣኦት [[እሽታር]] ይታወሱ ነበር። ስለ ተሙዝም ሞት በየአመቱ በብዙ ልቅሶ ማስታወሻ በዓል ይደረግ ነበር።