ከ«ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 11፦
ባሻ ኪዳኔ ከባላምባራስ ገረሱ ጋር ከሙሴ ቀስተኛ የተማረከውን አላስረክብም በማለታቸውና በሌላም ምክንያቶች ባለመስማማታቸው፤ በ[[ኅዳር]] ወር [[፲፱፻፴፩]] ዓ.ም. አባሎቻቸውን አስከትለው ወደ ትውልድ አገራቸው ወደቡልጋ ተጉዘው በአሥራ ሁለት ቀናቸውም ቡልጋ ገቡ። እዚሁም ከ[[ፊታውራሪ ኃይለማርያም ማናህሌ]] እና ከ[[ፊታውራሪ ተረፈ ማናህሌ]] ጋር ተቀላቅለው እስከ [[መጋቢት]] [[1931|፲፱፻፴፩]] ዓ.ም. ድረስ በውሽንግር፤ ጨፌ ዶንሳ ምሽግ፤ ነጭ ድንጋይ ምሽግ፤ ልዝብ ድንጋይ ከተባሉ ቦታዎች ላይ ከጠላት ኃይል ጋር ሲዋጉ ከርመው በመጋቢት ወር በሃገሩ ላይ ገብቶ በነበረው የ [[እንቅጥቅጥ በሽታ]] በጽኑ ታመው ከልዝብ ድንጋይ ምሽግና ቤቶች ነጭ ድንጋይ ጦስኝ ምሽግ ከወደምስራቅ ኮረማሽ መካከል ታመው ተኙ:: ወዲያው በሰኔ ወር ሦሥት አምባ ላይ ሰፍረው ሳሉ ጠላት በ[[ሦስት አምባ]]፤ በ[[ወይን አምባ]] እና በ[[ጦስኝ]] በኩል ወርዶ ሲከባቸው ባሻ ኪዳኔ ገመምተኛ ስለነበሩ መሮጥ አቅቷቸው ‘ተማረክ’ እያለ የከበባቸውን የጠላት ጦር እየተከላለከሉ ጫካ ገቡ የጠላትም ወታደሮች የገቡበት ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ባሻ ኪዳኔ ጎርፍ በጀለጣት ዛፍ ተንጠልጥለው ደፍጠው ሲጠባበቁ ጠላት ጫካውን በእሳት ነበልባል ግራና ቀኙን ሲያቃጥልው እሳቸው ያሉባት ሳትቃጠል ሊተርፉ ቻሉ። ከሦስት ቀንም በኋላ ጠላት ለቆ ሲሄድ ባሻ ኪዳኔ ከጅረት ወርደው ውሃ ሲጠጡ ደክመው ወድቀው ሳሉ ወንድማቸውና ሌሎች ሲፈልጓቸው በጥይት ያሉበትን አሳወቋቸውና መጥተው በቃሬዛ አዛውሯቸው፡
 
ከዚህ በኋላ ክረምቱን ቡልጋ ውስጥ በ[[ነጭ ድንጋይ]]፤ [[ፍልፍል አፈር]]፤ [[ጦስኝ ምሽግ]]፤ በ[[መስኖ]] ከነ[[ደጃዝማች ሀብተኃብተ ሥላሴ]]፤ ከነ[[ፊታውራሪ በለጠ ሳሴ]]ና [[ፊታውራሪ አጎናፍር]] ሌሎችም ስመጥሩ የቡልጋየ[[ቡልጋ]] ልጆች ጋር ሆነው ጠላትን ሲያጠቁና ሲከላከሉ ቆይተው በ[[መስከረም]] [[1932|፲፱፻፴፪]] ዓ.ም በ[[ሰገሌ]] በኩል ተጉዘው [[ገሊላ]] ከሚባል ሥፍራ ላይ ከራስከ[[አበበ አረጋይ|ራስ አበበ አረጋይ]] ጋር ሲቀላቀሉ ባሻ ኪዳኔ የ[[ግራዝማች]]ነት ማዕረግ ተሾሙ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከ”[[ጊዲዮን ፎርስ]]” (Gideon Force) ጋር ወደ[[ጎጃም]]ና ወደ[[ጎንደር]] እስከዘመቱ [[1933|፲፱፻፴፫]] ዓ.ም ድረስ ከራስ አበበ ጋር ጠላትን በየቦታው ሲዋጉ በአርበኝነት ቆዩ። ከብዙ ከተለያዩ ውጊያዎችና ጀብዱዎች በኋላ በ[[የካቲት]] [[1933|፲፱፻፴፫]] ዓ.ም [[መሶቢት]] ከሚባለው ቦታ ላይ በመሪነት የጠላትን ጦር ድል አድርገው ወደዋናው ሰራዊት ከተቀላቀሉ በኋላ ራስ አበበ የ[[ቀኛዝማች]]ነት ማዕረግ ሾሟቸው።
 
===የሰሜን ዘመቻ===