ከ«ኒኑስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
ሎሌ ማስተካከል: de:Ninos; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Ninus Rex.jpg|thumb|200px|ኒኑስ በሰዓሊው [[ጊዮም ሩዊ]] ዕይታ <br />('''1545''' ዓ.ም.)]]
 
'''ኒኑስ''' በጥንታዊ የ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ የ[[ነነዌ]] መስራችና የ[[አሦር]] ንጉስ ነበረ። ለዘመናዊ ሥነ ቅርስ የታወቀ አንድ ግለሰብ አይመስልም፤ ዳሩ ግን የአያሌ ታሪካዊ ወይም አፈ ታሪካዊ ግለሰቦች ትዝታ በአንድ ስም በግሪኮች በኋለኛ ዘመን እንደ ተዘከረ አሁን ይታስባል።
 
የንጉሥ ኒኑስና ሚስቱ ንግሥት [[ሴሜራሚስ]] ስሞች በጽሁፍ መጀመርያ የተገኘው [[ክቴስያስ ዘክኒዱስ]] (400 ዓክልበ. ገዳማ) በጻፈው በ[[ፋርስ]] አገር ታሪክ ነው። ክቴስያስ ለ[[2 አርጤክስስ]] (2 አርታሕሻጽታ) የመንግሥት ሀኪም ሆኖ የፋርስ ነገሥታት ታሪካዊ መዝገቦች አንብቤያለሁ ብሎ አሳመነ።<ref>''"Like a Bird in a Cage": The Invasion of Sennacherib'', Lester L. Grabbe (2003), p. 121-122</ref> ከዚህ በኋላ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] የክቴስያስን ወሬ አስፋፋ። የአለም ታሪክ ሊቃውንት እስከ [[1880ዎቹ]] ድረስ የኒኑስ ታሪክ ዕውነት መሆኑን ይቈጠሩት ነበር። በዚያን ጊዜ [[የኩኔይፎርም ጽሕፈት]] ፍች ስለ ተፈታ፣ በ[[ሜስፖጦምያ]]ና በነነዌ ብዙ ቅርሶችም በመገኘታቸው፣ የአሦር ትክክለኛ ታሪክ ዕውቀት ተጨመረልን።
 
ኒኑስ የ[[ቤሉስ]] ወይም [[ቤል]] ልጅ ተባለ፤ ይህም ምናልባት በሴማዊ ቋንቋ ሥር «ባል» (ጌታ) የመሰለ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። በ[[ካስቶር ዘሮድስ]] ዘንድ ኒኑስ ለ52 ዓመታት ነገሰ፤ ክቴስያስም እንዳለው መጀመርያው ዓመተ መንግሥቱ 2198 ዓክልበ. ነበረ። በ17 አመታት ውስጥ ኒኑስ በ[[አረቢያ]] ንጉስ አርያዎስ እርዳታ ምዕራብ [[እስያ]]ን በሙሉ እንዳሸነፈ ተብሏል። ከዚህ ቀጥሎ የ[[አርመን]] ንጉስ ባርዛኔስን (ይቅርታ የሰጠውን) እና የ[[ሜዶን]] ንጉስ ፋርኖስን (በስቅለት ይሙት በቃ የሰጠውን) ድል በማድረግ የአለም መጀመርያ ንጉሠ ነገስት እንደ ሆነ ተብሏል።
 
[[Fileስዕል:Ninus.png|thumb|left|300px|የኒኑስ መንግሥት ስፋት በዲዮዶሮስ ዘንድ]]
 
ግሪኮቹ እንደ ተረኩት፣ ይህ ኒኑስ በዙርያው ያሉትን እስያዊ አገሮች ከ[[ሕንድ]]ና ከ[[ባክትርያና]] በስተቀር በሙሉ አሸነፋቸው። ከዚያ ወዲያ ኒኑስ በ2 ሚሊዮን ወታደሮች ሠራዊት በባክትርያና ንጉሥ በኦክስያርቴስ ላይ ወረራ ጀመረ። አገሩ ሁሉ ቢወድቅም ዋና ከተማው [[ባክትራ]] ግን አልወደቀምና ሠራዊቱ ከበቡት። ባክትራን ሲከብቡት ኒኑስ የመኮነኑ [[ኦኔስ]] ሚስት ሴሜራሚስ አገኛትና ከባልዋ ነጥቆ እንደ ራሱ ሚስት ልትሆን ያዛት። ልጃቸው የኒኑስ ተከታይ [[ኒንያስ]] ሆነ።
 
ከ[[ሮማዊ]] ታሪክ ጸሃፊ [[ኬፋልዮን]] (120 ዓ.ም. ገደማ) ጀምሮ፣ አንዳንድ ታሪክ ሊቅ የኒኑስ ተቃዋሚ ኦክስያርቴስ ሳይሆን፣ በዕውነት የባክትርያ ንጉሥ [[ዞራስተር]] እንደ ነበር ጽፈዋል።
 
በ[[ቅሌሜንጦስ ጽሁፎች]] በአንዱ ዕትም፣ የኒኑስ መታወቂያ ከ[[ናምሩድ]] ጋራ አንድላይ ነው በማለት ደራሲው ይኸው ሰው የእሳት አምልኮት ለፋርሶች ያስተማረ ነው ይነግረናል። በ[[ኦሪት ዘፍትረት]] 10፡11-12 መሠረት የነነዌ መስራች የሴም ልጅ አሦር ቢባልም፣ በአንዳንድ ትርጉም ከ[[እብራይስጥ]] መጽሐፍ ቅዱስ፣ የነነዌ መስራች ናምሩድ እንደ ነበር ይመስላል።
 
በ[[19ኛው ክፍለ ዘመን]] ''[[ሁለቱ ባቢሎኖች]]'' የጻፈው [[አሌክሳንድር ሂስሎፕ]] ሃልዮ፣ የናምሩድና የኒኑስ (እንዲሁም የዞራስተር) መታወቂያ አንድ መሆኑ ዋና ነጥብ ነው።
 
ክቴስያስና ዲዮዶሮስ እንዳወሩት፣ ከኒኑስ ሞት በኋላ ሴሜራሚስ እንደ ገደለችው ተከሰሰች። እርስዋ ግን ታላቅ መቅደስ ግንብ በ[[ባቢሎን]] ለማስታወሻው አሠራች። እርስዋ በተጨማሪ በእስያ መጨረሻው ነፃ ንጉሥ በሕንድ ንጉሥ [[ስትራቶባቴስ]] ላይ ዘመቻ እንዳደረገች አወሩ። ነገር ግን ድል ሆና ለልጅዋ ለኒንያስ ዙፋኗን ተወች ነበር።
 
== ምንጮች ==
* [http://penelope.uchicago.edu/Thayer/E/Roman/Texts/Diodorus_Siculus/2A*.html#1 Full account in Diodorus]
<references/>
መስመር፡ 27፦
[[ang:Ninus]]
[[ca:Ninos]]
[[de:NinusNinos]]
[[el:Νινύας]]
[[en:Ninus]]