ከ«ደብረ ዳሞ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[Image:Debre Damo Acces.jpg|thumb|ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም መጓጓዣ መንገድ]]
'''ደብረ ዳሞ''' በ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው። ደብረ ዳሞ ከ[[አዲግራት]] በስተምዕራብ በመካከለኛው [[ትግራይ]] ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከ[[ቆዳ]] በተሰራ [[ገምድ]] ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይይዛል። የተሰራውም በ[[አቡነ አረጋዊ]] በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። [[ቶማስ ፓከናም]] የተባለው የታሪክ ተመራማሪ አምባው እንደ [[ወህኒ]]ና [[አምባ ግሸን]] ወንድ የነገስታት ዝርያወችን ለማሰሪያነት ያገለግል እንደነበር ትውፊት እንዳለ በጥናት ደርሶበታል። <ref>Thomas Pakenham, ''The Mountains of Rasselas'' (New York: Reynal & Co., 1959), pp. 79-86</ref> የገዳሙ ውጫዊ ወለሎች በጥንቱ ዘመን ዘዴ፣ የ[[ኖራ ድንጋይ]]ንና የጥድየ[[ጥድ]] እንጨትን በማፈራረቅ የተሰራ ነበር። ይህም በ[[ስነ ህንጻ]] ጥበበ [[አክሱም|አክሱማዊ]] ዘዴ አሰራር ይባላል።<ref>Pakenham, p. 85</ref>
 
[[Image:Debre Damo Church.jpg|thumb|left|265px|ደብረ ዳሞ ገዳም በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ዘዴ]]