ከ«ሰብለ ወንጌል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ ማስወገድ: en:Sabla wengel
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Libnadengel.jpg|300px|right|thumb| የንግስት ሰብለ ወንጌል ባል የነበሩት አጼ [[ልብነ ድንግል]] ]]
ንግስት '''ሰብለ ወንጌል''' የዓፄ [[ልብነ ድንግል]] ሚስት ስትሆን ከእናት ንግስት [[እሌኒ]] ሞት በሁዋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የእሌኒን እግር ተክታ ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራት ናት። በነበረችበት ዘመን፣ የ[[አህመድ ግራኝ]] ጦር በ[[ቱርክ]] ጠመንጃ አንጋቢወች ታግዞ ብዙ የኢትዮጵያን ክፍል በተቆጣጠረበት ዘመን ነው። በዚህ የጦርነት ዘመን የመጀምሪያ ልጇ ሲገደል አራተኛው ልጇ ፣ የወደፊቱ [[አጼ ሚናስ]] ተማርኮ ወደ [[የመን]] ተግዟል። ይህ የተማረከው ልጇ በሁዋላ በእስረኞች ቅይይር ተመልሷል። ሰብለ ወንጌል የአዳሎችን ጦር እስከመጨረሻው የታገለችን ባሏ በ[[ደብረ ዳሞ]] ([[ትግራይ]]) በ1540 በህመም ከሞተ በኋላ ሁሉ እጅ ሳትሰጥ ታግላ አታግላለች።
 
ከባሏ ሞት ኋላ ሁለተኛ ልጇ አጼ [[ገላውዲወስ]] ንጉስ ሆነ። ይህ ልጇ በደቡብ ክፍል ውጊያ ከፍቶ በመታገል ላይ እያለ በ[[ክሪስታቮ ደጋማ]] የሚመራው የ[[ፖርቹጋል]] ጦር [[ምጽዋ]] ላይ አረፈ። ከተራራው ምሽጓ ላይ ሆነ ከፖርቹጋሎቹ ጋር ከተደራደረች በኋላ ከፖርቹጋሎቹ የጦር ቀጠና ጋር ተቀላቀለች። እበቅሎዋ ላይ ቁጭ ብላም የፖርቹጋሎቹን 400 ሰራዊት በፊቱዋ ሲያልፍ እንደመረመረች ታሪክ ያትታል።