ከ«ኪሽ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ ማስተካከል: nl:Kiš
No edit summary
መስመር፡ 3፦
'''ኪሽ''' የ[[ሱመር]] (የዛሬው [[ኢራቅ]]) ጥንታዊ ከተማ ነበረ።
 
[[የሱመር ነገሥታት ዝርዝር]] በተባላው ሰነድ ዘንድ፣ ከ[[ማየ አይኅ]] በኋላ መጀመርያው ነገሥታት የነበሩበት ከተማ ኪሽ ሲሆን መጀመርያው ንጉሣቸው [[ጁሹርጙሹር]] ነበር። የጁሹርምየጙሹርም ተከታይ ስም [[ኩላሢና-ቤል]] ሲባል፣ ይህ ስም ግን በ[[አካድኛ]] «ሁላቸው ባል (ሆኑ)» የሚለው ዓረፍተ ነገር ነው። ስለዚህ ምናልባት ይህ ስም መሃል ሥልጣን አለመኖሩን ለማመልከት እንደ ጠቀመ ይታስባል። የሚከተሉት 9 ስሞች ደግሞ ሁላቸው በአካድኛ የእንስሳት ስሞች ናቸው (ለምሳሌ [[ዙቃቂፕ]] («ጊንጥ»)። አካድኛ [[ሴማዊ ቋንቋ]] እንደ መሆኑ መጠን፣ ይህ ከጥንት ጀምሮ የኪሽ ኗሪዎች በሰፊው ሴማውያን እንደ ጠቀለሉ ያሳያል።<ref>[http://books.google.com/books?id=slR7SFScEnwC&pg=PA100&dq=kish+%22semitic+names%22 Cambridge Ancient History, p. 100]</ref> ሆኖም ለነኚህ ቅድመኞች ነገሥታት አንዳችም ቅርስ ስላተገኘላቸው፣ ታሪካዊ መሆናቸው አጠያያቂ ነው።
 
በዝርዝሩ ላይ 12ኛው የኪሽ ንጉሥ፣ [[ኤታና]]፣ «ወደ ሰማይ ዐርጐ ውጭ አገሮችን ሁሉ ያሠለጠነው» ይባላል። ለርሱም ኅልውና የቅርስ ማረጋገጫ ገና ባይገኝም፣ ስሙ ከአንዳንድ ሌላ የትውፊት ጽላት ይታወቃል። አንዳንዴም ይህ ኤታና የኪሽ መጀመርያው ንጉሥና መስራች ይባል ነበር።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ኪሽ» የተወሰደ