ከ«ጊዮርጊስ አህዮቹን ይዞ የወረደ ጊዜ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «ሴትዮዋ በእንስራ ውሃ ተሸክማ ቁልቁለት ትወርድ ነበርና ቁልቁለቱ በጣም ቁልቁል ከመሆኑ የተነሳ ዘጭ ...»
(No difference)

እትም በ16:50, 5 ሴፕቴምበር 2010

ሴትዮዋ በእንስራ ውሃ ተሸክማ ቁልቁለት ትወርድ ነበርና ቁልቁለቱ በጣም ቁልቁል ከመሆኑ የተነሳ ዘጭ ዘጭ ዘጭ እያለች በፍጥነት እንድትወርድ ያስገድዳታል። በዚህ ጊዜ ፈሷ ያመልጣትና ዛጥ ዛጥ... ዛጥ... ታደርገዋለች፤ ድምጿን ክፍ አድርጋ "አንተ ጊዮርጊስ አሁንስ እንደ አህዮቹ ልታደርገኝ ነው" አለች። "እህህ ..." እያለ ጉሮሮውን የሚጠራርግ ሰው ድምጽ ሰምታ ዘወር ስትል አለቃን አየችና "ውይ! አለቃ መቼ መጡ?" አለቻቸው። እሳቸውም "ጊዮርጊስ አህዮቹን ይዞ የወረደ ጊዜ" ብለው መለሱላት።