ከ«አብርሀም ሊንከን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ ማስተካከል: ang:Abraham Lincoln
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Abraham Lincoln head on shoulders photo portrait.jpg|200px|thumb|አብርሀም ሊንከን]] '''አብርሀም ሊንከን''' ([[እንግሊዝኛ]]፦ ''Abraham Lincoln''፣ [[የካቲት 6]] ቀን [[1801]] ዓ.ም. - [[ሚያዝያ 8]] ቀን [[1857]] የኖሩ) ከ[[1853]] እስከ 1857 ዓ.ም. ድረስ 16ኛው [[የአሜሪካ ፕሬዚዳንት]] ነበሩ። በ1857 አ.ም. ከብሔራዊው ጦርነት ቀጥሎ ገና ፕሬዚዳንት እየሆኑ ተተኩሰው ተገደሉ።
 
የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በጥጋት ያስተምር ነበር። በ[[1826]] ለ[[ኢሊኖይ]] ክፍላገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጉልበት አጥነው የሕግ አዋቂ ሆኑ። ከ[[1829]] ዓ.ም. ጀምሮ የ[[ባርነት]] ተቃዋሚ ሆነ። ከ[[አፍሪካ]] የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በ[[ግብርና]] መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛትክአሸነፉ። ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ[[1834]] ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን [[ሜሪ ቶድ]]ን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር በመኖር ትንሽ ተቸግራ ሩቅ ባልሆነ ግዜ ውስጥ ግን ተለመደችና በተከተሉት አመታት ላይ 4 ወንድ ልጆችን ወለዱ።
 
በ[[1838]] ዓ.ም. የአሜሪካ ፕሬዚዳንት [[ጄምስ ፖልክ]] በ[[ሜክሲኮ]] ላይ ጦርነት ባደረገ ጊዜ አብርሀም ሊንከን የዚህን ጦርነት ተቃዋሚ ነበሩ። በ[[1846]] ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን [[ሪፐብሊካን ፓርቲ (አሜሪካ)|ሪፐብሊካን ፓርቲ]] መሠርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና አጫወቱ። በ[[1852]] ፕሬዚዳንት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በ[[ጥቅምት 28]] ቀን [[1853]] ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ።
 
ይህም የሆነ የሕዝቡ ብዛት በአገሩ ስሜን እየኖረ የሬፑብሊካን ደጋፊዎች ነበሩ። በስሜኑ ክፍላገሮች ደግሞ፣ ባርነት ከዚህ በፊት ተክለክሎ ነበር። በአሜሪካ ደቡብ በተገኙ ክፍላገሮች ግን ባርነት ገና የተለመደ ከመሆኑ በላይ በ[[ጥጥ]] የተመሠረተው የምጣኔ ሀብታቸው አስፈላጊነት መሰላቸው። ስለዚህ የባርነት ተቃዋሚ ሊንከን ፕሬዚዳንት መሆኑ በደቡብ ያሉት ክፍላገሮች ከአሜሪካ መገንጠላቸው ማለት ነበር። እንዲሁም ከምርጫው ቶሎ ተቀጥሎ ማዕረጉንም እንኳን ገና ሳይይዙ፣ [[ሳውስ ካሮላይና]] በ[[ታኅሣሥ 12]] ቀን 1853 ዓ.ም. መገንጠሏን አዋጀች። በጥቂት ግዜ ውስጥ ሌሎች የደቡብ ክፍላገሮች እንዲህ አዋጁና በ[[ጥር 25]] ቀን [[ቴክሳስ]] 7ኛው ሆነ። ከዚያ ቀጥሎ እነዚህ 7 ክፍላገሮች በ[[ሞንትጎመሪ፣ አላባማ]] ተባብረው አዲሱ መንግሥት [[የአሜሪካ ኮንፌዴራት ክፍላገሮች]] (CSA) ተባሉ። በ[[የካቲት 26]] ሊንከን የፕሬዚዳንትነቱን ማዕረግ በተቀበሉበት ቀን አገሩ በተግባር በ2 ተከፋፍሎ ነበር። የደቡብ ፕሬዚዳንት [[ጄፈርሰን ዴቭስ]] ሆኑ። የደቡብ ክፍላገሮች ለጦርነት ተዘጋጁና ምሽጎች ከUSA ሠራዊት ሊይዙ ጀመር። በ[[ሚያዝያ 5]] ቀን [[ፎርት ሰምተር]] ምሽግ በሳውስ ካሮላይና በግፍ ስለ ተያዘ ጦርነቱ ጀመረ። ስለዚህ ሊንከን ከስሜኑ 75,000 ሰዎች ለዘመቻ ጠሩ። ከዚህ በኋላ ሌላ 4 ደቡብ ክፍላገሮች ተገንጥለው ለCSA ተጨመሩ። የደቡብ ዋና ከተማ ለ[[ዋሺንግተን ዲሲ]] ቅርብ ወደ ሆነው ወደ [[ሪችሞንድ፣ ቪርጂንያ]] ተዛወረ።