ከ«ኪሽ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ መጨመር: en:Kish (Sumer)
ሎሌ ማስተካከል: nl:Kiš (Sumer); cosmetic changes
መስመር፡ 3፦
'''ኪሽ''' የ[[ሱመር]] (የዛሬው [[ኢራቅ]]) ጥንታዊ ከተማ ነበረ።
 
[[የሱመር ነገሥታት ዝርዝር]] በተባላው ሰነድ ዘንድ፣ ከ[[ማየ አይኅ]] በኋላ መጀመርያው ነገሥታት የነበሩበት ከተማ ኪሽ ሲሆን መጀመርያው ንጉሣቸው [[ጁሹር]] ነበር። የጁሹርም ተከታይ ስም [[ኩላሢና-ቤል]] ሲባል፣ ይህ ስም ግን በ[[አካድኛ]] «ሁላቸው ባል (ሆኑ)» የሚለው ዓረፍተ ነገር ነው። ስለዚህ ምናልባት ይህ ስም መሃል ሥልጣን አለመኖሩን ለማመልከት እንደ ጠቀመ ይታስባል። የሚከተሉት 9 ስሞች ደግሞ ሁላቸው በአካድኛ የእንስሳት ስሞች ናቸው (ለምሳሌ [[ዙቃቂፕ]] («ጊንጥ»)። አካድኛ [[ሴማዊ ቋንቋ]] እንደ መሆኑ መጠን፣ ይህ ከጥንት ጀምሮ የኪሽ ኗሪዎች በሰፊው ሴማውያን እንደ ጠቀለሉ ያሳያል።<ref>[http://books.google.com/books?id=slR7SFScEnwC&pg=PA100&dq=kish+%22semitic+names%22 Cambridge Ancient History, p. 100]</ref> ሆኖም ለነኚህ ቅድመኞች ነገሥታት አንዳችም ቅርስ ስላተገኘላቸው፣ ታሪካዊ መሆናቸው አጠያያቂ ነው።
 
በዝርዝሩ ላይ 12ኛው የኪሽ ንጉሥ፣ [[ኤታና]]፣ «ወደ ሰማይ ዐርጐ ውጭ አገሮችን ሁሉ ያሠለጠነው» ይባላል። ለርሱም ኅልውና የቅርስ ማረጋገጫ ገና ባይገኝም፣ ስሙ ከአንዳንድ ሌላ የትውፊት ጽላት ይታወቃል። አንዳንዴም ይህ ኤታና የኪሽ መጀመርያው ንጉሥና መስራች ይባል ነበር።
 
በዝርዝሩ 21ኛው ንጉሥ፣ [[ኤንመባራገሲ]]፣ «የ[[ኤላም]]ን ጦር ያጠፋው» ይባላል። የርሱ መንግሥት መጀመርያው በ[[ሥነ ቅርስ]] የተረጋገጠ ነው። እንደገና በሌላ ትውፊት ይታወቃል፤ እርሱና ልጁ [[አጋ]] የኪሽ ንጉሶች በሆኑበት ወቅት፣ ጣውንታቸው የ[[ኡሩክ]] ነገሥታት [[ዱሙዚድ አሣ አጥማጁ]] እና [[ጊልጋመሽ]] እንደ ነበሩ ይባላል።
 
በዚህ ድሮ ዘመን አንዳንድ የኪሽ ንጉሥ ከሥነ ቅርስ ቢታወቅም በ''ሱመር ነገሥታት ዝርዝር'' ግን የሉም። ከነዚህም መካከል የኪሽ ንጉሥ ኡቱግ ወይም ኡሁብ [[ሐማዚ]]ን እንዳሸነፈ የሚል ቅርስ አለ፤ ደግሞ የኪሽ ንጉሥ [[መሲሊም]] መቀደሶችን በ[[አዳብ]]ና በ[[ላጋሽ]] ከተሞች እንዳሠራ የሚሉ ቅርሶች አሉ።
 
በኋላ የኪሽ ሥልጣን ደክሞ፣ ከተማው ለሌሎች የከተማ-አገር መንግሥታት ይወድቅ ነበርና አይነተኛ ከተማ እንደ መሆኑ፣ «የኪሽ ንጉሥ» የሚለውም አርእስት እንደ ትልቅ ማዕረግ ተቆጥሮ፣ እነዚህ የሌሎች ከተሞች ነገሥታት ለራሳቸው ወገን «የኪሽ ንጉሥ» ይባሉ ጀመር። ለምሳሌ የ[[ኡር]] ንጉሥ [[መስ-አኔ-ፓዳ]] «የኪሽ ንጉሥ» ደግሞ ይባል ነበር። ታዋቂው [[የአካድ መንግሥት]] ንጉስ [[ታላቁ ሳርጐን]] ከኪሽ ዙሪያ ነበር።
 
[[Imageስዕል:Murex Rimush Louvre AO21404.jpg|thumb|left|280px|በዚህ ጥንታዊ ዛጎል የተቀረጸው ጽሕፈት በአካድኛ «ሪሙሽ የኪሽ ንጉሥ» ይላል።]]
 
== የውጭ መያያዣዎች ==
 
<references/>
 
* [http://libmedia.cc.stonybrook.edu/cgi-bin/showfile.exe?CISOROOT=/amar&CISOPTR=4635&filename=5163.pdf] McGuire Gibson, The city and Area of Kish, Coconut Grove, 1972
* [http://www.archive.org/download/sumerianpalaceac12mack/sumerianpalaceac12mack.pdf] E. Mackay, Report on the Excavation of the "A" Cemetery at Kish, Mesopotamia, Pt. 1, A Sumerian Palace and the "A" Cemetery , Pt. 2 (Anthropology Memoirs I, 1-2),Chicago: Field Museum,1931
* [http://oi.uchicago.edu/pdf/mad5.pdf] I. J. Gelb, Sargonic Texts in the Ashmolean Museum, Oxford, Materials for the Assyrian Dictionary 5, The University of Chicago Press, 1970 ISBN 0-226-62309-2
* [http://www.fieldmuseum.org/kish/introduction.asp Online Kish Collection at the Field Museum]
* [http://www.youtube.com/watch?v=7kKeiRdXDfw YouTube video on Field Museum Kish effort]
* [http://oi.uchicago.edu/gallery/asp_meso_kish/ Kish Site photographs at Oriental Institute of Chicago]
 
[[መደብ:የቀድሞ ከተሞች]]
መስመር፡ 46፦
[[ka:ქიში]]
[[ko:키시]]
[[nl:KishKiš (Sumer)]]
[[no:Kish]]
[[oc:Kish]]
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ኪሽ» የተወሰደ