ከ«ወንጌል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ « ወንጌል ኢቫንግሊካል ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም የምስራች ማለት ነው። ኢየሱስ ክ...»
(No difference)

እትም በ06:11, 28 ኦገስት 2010

ወንጌል ኢቫንግሊካል ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም የምስራች ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸው ትምሀርቶች የተመዘገቡበት መጽሐፍት ወንጌል በመባል ይታወቃሉ። ወንጌል ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ሲሆን አራት መጽሐፍትን ያጠቃልላል። የማቴዎስ ወንጌል፤ የሉቃስ ወንጌል፤ የማርቆስ ወንጌልና የዮሐንስ ወንጌል። እነዚህ ወንጌላት ስማቸውን ያገኙት ከጸሐፊዎቻቸው ሲሆን የያዙት ቃል የኢየሱስ ክርስቶሰን ትወልድ፤ ትምህርት፤ ሞትና ትንሳዔ ነው። ሶስቱ ወንጌላት ማለትም የማቴዎስ፤የሉቃስና የማርቆስ ወንጌል ተመሳሳይ የሆኑ ብዙ ታምራቶችንና ክስተቶችን ይዘው ይገኛሉ። የዮሓንስ ወንጌል ደግሞ በአብዛኛው ያካተተው የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነትና የአብ ልጂነት የሚያብራራ መልእክት ነው።

ብዙ ምእራፎችን የያዘው ወንጌል የማቴዎስ ወንጌል ሲሆን 27 ምእራፎች አሉት ትንሽ ምእራፍ ያለው ደግሞ የማርቆስ ወንጌል ነው ይኸውም 16 ምእራፎች አሉት። ወንጌል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ክብር የሚሰጠውና አብዝቶ የሚነበብ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ነው። በቅዳሴ ጊዜ ፤ በሌሊት ጸሎትና በጉባያት ወቅት ወንጌል ይነበባል።