ከ«አቅም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ መጨመር: simple:Energy
ሎሌ መጨመር: mg:Angôvo; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Simple_harmonic_oscillator.gif|thumb|right|ስፕሪንጉ በተለጠጠ ጊዜ እቃውን ወደ ላይ የመሳብ [[አቅም]] አለው እንላለን። እቃው ወደላይ ሲንደረደር ሄዶ ስፕሪንጉን ሲጨምቀው፣ ስፕሪንጉና የዕቃው እምቅ አቅም እቃውን ወደምድር የመወርውር [[አቅም]] አላቸው እንላለን። ]]
'''አቅም''' (Energy) በፊዚክስ ጥናት ሲተረጎም ያንድ ሰው፣ እንስሳ፣ ቁስ፣ [[ስራ]] የመሰራት ችሎታ ወይም ለውጥ የማምጣት ችሎታ ማለት ነው። አቅም የሚለካው በጁል (Jules) ነው።
 
== ሳይንሳዊ አቅም ==
 
ሳይንሳዊ አቅም በሁለት ይክፈላል
 
* [[ተንቀሳቃሽ አቅም]] (Kinetic energy)
:: የምንለው አንድ ቁስ በመንቀሳቀሱ ምክያት ስራ ለመሰራት የሚያዳብረው አቅም ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ ድንጋይ ቢወረወር ያ ድንጋይ በንቅስቃሴ ላይ እያለ ጠርሙስ ቢያጋጥመው ያን ጠርሙስ የመስበር ስራ ያካሂዳል። በዚ ምክንያት የተወረወረ ድንጋይ ተንቀሳቃሽ አቅም አለው እንላለን።
* [[እምቅ አቅም]] (Potential energy)
:: የምንለው ደግሞ አንድ ቁስ ወይም የቁስ ስርዓት በ[[ጉልበት ሜዳ]] ውስጥ ባለው አቀማመጥ ምክንያት በውስጡ የተከማቸ አቅም ነው። ለምሳሌ የመሬት ስበት በምድራችን ዙሪያ የመሳብ ጉልበት ሜዳ ፈጥሮ አለ። በዚህ ምክንያት አንድን ድንጋይ ከመሬት አንስተን ብንይዝ በዚያ ዲንጋይ ላይ እምቅ አቅም ይኖራል ምክናይቱም ድንጋዩን ስንለቀው ባለው እምቅ አቅም ምክንያት አንድን ጠርሙስ መስበር ይችላል።
 
== አቅም አይጠፋም ==
 
ከላይ እንዳየነው ሁለት አይነት የአቅም አይነቶች አሉ። በነዚህ ስር የሚተዳደሩ ሌሎች አይነቶችም አሉ። ለምሳሌ የ"ኮረንቲ አቅም"፣ የ"ማግኔት አቅም"፣ የ"ድምጽ አቅም"፣ ወዘተ.. ነገር ግን አንዱ አይነት አቅም ወደ ሌላ አቅም ሲቀየር ወይም አይጨምርም ወይም ደግሞ አይቀንስም። የአቅሙ መጠን ምንግዜም አንድ አይነት ነው። በሌላ ቋንቋ፦
 
'''ምንጊዜም አቅም አይፈጠርምም አይጠፋምም።'''
 
=== ምሳሌ ===
:# ሲጀመር የአንድ ቁስ አቅም ተለካ እንበል። ሲለካ 50 ጁል ነው እንበል።
# እንበልና የዚህ እቃ አቅም እምቅ ነበር ነገር ግን በመንቀሳቀሱ ወደ ተንቀሳቃሽ አቅም ተቀየረ።
መስመር፡ 24፦
በዚህ ጊዜ ሲጀመርና ሲያልቅ ያለው አቅም እኩል ሆኖ ይገኛል። ይኽውም 50 ጁል ነው ማለት ነው።
 
=== አዲሱ የ"አቅም አይጠፋም" ህግ ===
 
በአሁኑ ዘመን ሳይንቲስቶች አንድን [[ቁስ አካል]] ወደ [[አቅም]] በ[[ኑክልያር መበታተን]] እና [[ኑክሊያር መገጣጠም]] መለወጥ እንደሚቻል ደርሰውበታል። በዚህ ምክንያት የ[[አቅም አይጠፋም]] ህጉ ይህን ጉዳይ ለማስተናገድ ሲባል የ[[ቁስና አቅም አይጠፋም]] ህግ ብለውታል።
 
 
== የአቅም አይነቶች ==
ከብዙ በጥቂቱ ...
* [[ኮረንቲ|የኮረንቲ አቅም]]
* [[ብርሃን|የብርሃን አቅም]]
* [[ሙቀት| የሙቀት አቅም]]
* [[ውስጣቂ አቅም]]
* [[የድምጽ አቅም|ድምጽ]]
መስመር፡ 43፦
* [[የእንቅስቃሴ አቅም]]
 
== አቅምን መለኪያ ==
ከላይ እንደተገለጸው አቅም ይለካል። ይህም በቁጥር ይተመናል። የአቅም መለኪያ ዩኒት ጁል (J) ይባላል። አንድ ጁል ከአንድ ኒውተን ሜትር (1Nm) ወይም ( 1 kg m<sup>2</sup> s<sup>−2</sup>) ጋር እኩል ነው።
 
[[መደብ : ሳይንስ ]]
 
 
[[መደብ : ሳይንስ ]]
 
[[af:Energie]]
Line 104 ⟶ 102:
[[lt:Energija]]
[[lv:Enerģija]]
[[mg:Angôvo]]
[[mk:Енергија]]
[[ml:ഊർജ്ജം]]