ከ«ሙሴ ቀስተኛ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ሙሴ ቀስተኛ (ጣልያንኛ፡ Sebastiano Castagna)''' ይሄ ሰው በ[[አድዋ ጦርነት]] ኢትዮጵያን የ[[ጣልያን]] መንግሥት አገራችንን በቅኝ ግዛትነት ለመግዛት ከገቡት ወታደሮች አንዱ ሲሆን፣ ለወረራ የመጣው የጠላት ኃይል በ[[ዳግማዊ ምኒልክ|ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ]] እና በሠራዊታቸው ቆራጥነት አድዋ ላይ ድል ሲሆን ተማርኮ የቀረ ኢጣልያዊ ሰው ነው።
 
ሙሴ ቀስተኛ (ሴባስቲያኖ ካስታኛ) በ[[1860|፲፰፻፷]] ዓ/ም በ [[ሲሲሊ]] ደሴት አይዶኔ በሚባል ሥፍራ ተወለደ። በእርግጠኛነት እንዴት እና ለምን የ[[ጣልያን]]ን የጦር ሠራዊት እንደተቆራኘ መቼ፣ ከማን ሠራዊት ጋር፣ የትኛው ወደብ ላይ ኢትዮጵያ ላይ ለመዝመት እንደመጣ ባይታወቅም፤ በ[[ዳግማዊ ምኒልክ|ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ]] ዘመን ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛት ለማድረግ ከመጣው የጣልያን ጦር ጋር በወጥቶ አደርነት መጥቶ፣ [[አድዋ]] ላይ ድሉ የ[[ኢትዮጵያ]] ሲሆን ሙሴ ቀስተኛ በምርኮኛነት እዚያው ከቀሩት የጣልያን ወጥቶ አደሮች አንዱ እንደሆነ በታሪክ ተመዝግቧል።
 
ከተማረከም በኋላ በተግባረ ዕድ ሞያው ታዋቂነትን አትርፎ በምህንድስና ተግባራት እንደተሰማራና የ[[ደስታ ዳምጠው|ራስ ደስታ ዳምጠው]]ን አክስት ወይዘሮ በላይነሽን አግብቶ ማሪያ እና ጁሴፒና የተባሉ ሁለት ሴት ልጆች ወልደውለታል። <ref> www.quiaidone.it/giornalino/Gennaio2009.pdf sebastiano castagna</ref> ኢትዮጵያም ውስጥ እስከ ሁለተኛው የ[[ፋሽሽትፋሽስት ኢጣልያ]] ወረራ ድረስ እንደኖረ እና በወረራውም ጊዜ በአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ [[አርበኛ]] እጅ ሕይወቱን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳጣ ስለሱ ከተጻፉ ጥቂት ታሪካዊ መሥመሮች ላይ እንገነዘባለን።
ይሄ ሰው በአገራችን የታሪክ ዘገባዎች ላይ፣ ምናልባትም በታሪካችን ላይ በተጫወተው ሚና ረገድ በቂም ባይሆንም፣ ‘ብቅ፣ ጥልቅ’ እያለ ሲመዘገብ እናገኘዋለን። ስለዚህ ሰው አሟሟት ፀሐፊው በልጅነት ዘመን ያጠናው በመሆኑ ስለሰውዬው ማንነት እና አመጣጥ ለመመርመር ላደረገው ጥረት መነሻ ነው።