ከ«ሙሴ ቀስተኛ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦
ሙሴ ቀስተኛ (ሴባስቲያኖ ካስታኛ) በ[[1860|፲፰፻፷]] ዓ/ም በ [[ሲሲሊ]] ደሴት አይዶኔ በሚባል ሥፍራ ተወለደ። በእርግጠኛነት እንዴት እና ለምን የ[[ጣልያን]]ን የጦር ሠራዊት እንደተቆራኘ መቼ፣ ከማን ሠራዊት ጋር፣ የትኛው ወደብ ላይ ኢትዮጵያ ላይ ለመዝመት እንደመጣ ባይታወቅም፤ በ[[ዳግማዊ ምኒልክ|ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ]] ዘመን ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛት ለማድረግ ከመጣው የጣልያን ጦር ጋር በወጥቶ አደርነት መጥቶ፣ [[አድዋ]] ላይ ድሉ የ[[ኢትዮጵያ]] ሲሆን ሙሴ ቀስተኛ በምርኮኛነት እዚያው ከቀሩት የጣልያን ወጥቶ አደሮች አንዱ እንደሆነ በታሪክ ተመዝግቧል።
 
ከተማረከም በኋላ በተግባረ ዕድ ሞያው ታዋቂነትን አትርፎ በምህንድስና ተግባራት እንደተሰማራና የ[[ደስታ ዳምጠው|ራስ ደስታ ዳምጠው]]ን አክስት ወይዘሮ በላይነሽን አግብቶ ማሪያ እና ጁሴፒና የተባሉ ሁለት ሴት ልጆች ወልደውለታል። <ref> www.quiaidone.it/giornalino/Gennaio2009.pdf sebastiano castagna</ref> ኢትዮጵያም ውስጥ እስከ ሁለተኛው የ[[ፋሽሽት ኢጣልያ]] ወረራ ድረስ እንደኖረ እና በወረራውም ጊዜ በአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ [[አርበኛ]] እጅ ሕይወቱን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳጣ ስለሱ ከተጻፉ ጥቂት ታሪካዊ መሥመሮች ላይ እንገነዘባለን።
ይሄ ሰው በአገራችን የታሪክ ዘገባዎች ላይ፣ ምናልባትም በታሪካችን ላይ በተጫወተው ሚና ረገድ በቂም ባይሆንም፣ ‘ብቅ፣ ጥልቅ’ እያለ ሲመዘገብ እናገኘዋለን። ስለዚህ ሰው አሟሟት ፀሐፊው በልጅነት ዘመን ያጠናው በመሆኑ ስለሰውዬው ማንነት እና አመጣጥ ለመመርመር ላደረገው ጥረት መነሻ ነው።
መስመር፡ 17፦
==የፋሽሽት ወረራ ዘመን==
 
በ[[ጥቅምት]] ወር [[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ/ም ወረራው ሲጀመር የኢትዮጵያ ወጥቶ አደሮች እና አርበኞች የጠላትን ጦር ለመከላከል በሰሜን፤ በደቡብ፤ በምሥራቅ እና በምዕራብ ግንባሮች ተሠማርተው የተቻላቸውን ያህል ተቋቋሙ። ሆኖም የፋሽሽት ሠራዊት በዘመናዊ መሣሪያ እና የመርዝ ቦንብ አይሎባቸው በግንባር ለግንባር ግጥሚያ ይሸነፉና ንጉሠ ነገሥቱም በ[[ግንቦት]] ወር ተሰደው ወደ [[እንግሊዝ]] አገር ሄዱ። አገሪቷም በጣልያን ቁጥጥር ስር አደረች። የ[[ግራዚያኒ]] ሠራዊት ግን በ[[ደቡብ]] ግንባር [[ደስታ ዳምጠው|ራስ ደስታ ዳምጠው]] እና [[ደጃዝማች በየነ መርዕድ]] ፤ በ[[ምዕራብ]] የባላምባራስ [[ገረሱ ዱኪ]] አርበኞች በሰሜን [[ሸዋ]] ደግሞ የባላምባራስ [[ራስ አበበ አረጋይ|ራስ አበበ አረጋይ]] ሠራዊት አልበገር ብለው አስቸግረውት ቆዩ።
 
ግራዚያኒ በድርድር እነኚህን መሪዎች ለማስገባት ባደረገው ጥረት መልእክተኛና ሰላይ አድርጎ የመረጠው የኢትዮጵያውያንን ባህል ለ አርባ ዓመታት ያጠናውንንና የራስ ደስታን አክስት ያገባውን ይሄንኑ ሙሴ ቀስተኛን ነበር።
መስመር፡ 23፦
በዚህ ዓላማ መጀመሪያ የተላከውም ወደ ራስ ደስታ ዳምጠው ሲሆን፣ [[ታኅሣሥ 19|ታኅሣሥ ፲፱]] ቀን [[1929|፲፱፻፳፱]] ዓ/ም በ[[ባሌ]] ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ቡላንቾ (አርበጎና) የሚባል ሥፍራ ላይ ሁለቱ ተገናኝተው ለሁለት ሰዓት ያህል ተወያዩ።<ref> Sbacchi(1997) p176</ref> ቀስተኛ ከዚህ ድርድር በኋላ እንደገመተው፣ ራስ ደስታ እጃቸውን እንደሚሰጡና የጭፍሮቻቸውን፣ በተለይም የጣልያንን ወገን ከድተው ከሳቸው ጦር ጋር የተቀላቀሉትን ኤርትራውያን እስከሚያሳምኑ ድረስ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል በሚል ግምገማ ነው። ራስ ደስታ [[የካቲት 15|የካቲት ፲፭]] ቀን [[ቡታጅራ]] አካባቢ ላይ በ[[ትግራይ]] ተውላጅ ደጃዝማች ተክሉ መሸሻ ተይዘው በጠላት እጅ ወዲያው ተረሽነው ሞቱ።
 
የሙሴ ቀስተኛ ስም በታሪካችን ዘገባ ላይ እንደገና ብቅ የሚለው በ [[ግንቦት]] ወር [[1930|፲፱፻፴]] ዓ/ም ላይ ሲሆን አሁንም እንደቀድሞው የግራዚያኒ መልእክተኛና ሰላይ በመሆን ለዕርቅ ስምምነት ከ [[አበበ አረጋይ|ራስ አበበ አረጋይ]] ጋር [[ግንደበረት]] ላይ ተገናኝቶ ለግራዚያኒ አርበኞቹ ለመስማማት የሚፈልጉ መሆናቸውን አስታወቀ። የሠራዊቱንም ብዛት በተመለከተ የስለላ ዘገባውን ለግራዚያኒ አስታውቆ በተከተለው የፋሽሽት ጥቃት ብዙ ኢትዮጵያውያን አርበኞት አልቀዋል።
 
ሦስተኛውና የመጨረሻው ተልዕኮው በ [[ጥቅምት]] ወር [[1931|፲፱፻፴፩]] ዓ/ም ሲሆን [[በዳቄሮ]] በሚባል ሥፍራ ላይ ወደነበሩት ባላምባራስ (በኋላ ደጃዝማች) [[ገረሱ ዱኪ]] ነበር። እዚህ ሥፍራ ላይ ከሦስት ባላባቶች ጋራ የመጣው ቀስተኛ የሰባ አንድ ዓመት ሽማግሌ፣ ነጭ ጸጉር እና ባለሙሉ ጺማም ሲሆን አርበኞቹን ሰብስቦ በተጣራ አማርኛ ‘ንጉሠ ነገሥታችሁ እንኳን ትቷት የሄደውን አገር እናንተ በዚህ በልጅነት እድሜያችሁ ቅማል ወሯችሁ የማይቀርላችሁን ሞት ገደል ለገደል ከምታባርሩ ይልቅ ገብታችሁ ከኢጣልያ ጋር አገራችሁን በልማት ብታገለግሉ አይሻልም ወይ? መሣሪያችሁን አስረክባችሁ የገባችሁ እንደሆነ ኢጣልያ ትምራችኋለች፤ ሹመት እና ሽልማትም ትሰጣችኋለች” ብሎ ሲሰብካቸው ወጣት አርበኞቹም ቀደም ሲል በ፲፱፻፴ ዓ.ም ይኼው ሰላይ ወደ ራስ አበበ አረጋይ ዘንድ ሄዶ የጦሩን ኃይል ከሰለለ በኋላ ብዙ አርበኛ እንዳስፈጀ ሰምተው ስለነበር እነሱንም እንደዚሁ ለማስፈጀት እንደመጣ ተገንዝበውታል። ከሰበካው በኋላ ወደ እኩለ ቀን ሲሆን ተበተኑ።