ከ«ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከስደት ሲመለሱ ‘ፀሐፌ ትዕዛዝ’ ተብለው የጽሕፈት ሚንስቴር ሆነው ይሾማሉ። በተለምዶው ስርዓት የጽሕፈት ሚኒስቴሩ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥታዊ መዝገቦች ጸሐፊ እና ጠባቂ ሲሆን፣ ዐዋጆች፤ ትዕዛዛት እና መንግሥታዊ ሰነዶችም በዚሁ ሰው በኩል ያልፋሉ። ይሄ ማለት ደግሞ ከላይ እንደሠፈረው፣ ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደመስቀል በ”ዝክረ ነገር” ላይ “ትንሹም ትልቁም ንጉሠ ነገሥቱ የእግዚአብሔር ተወካይ ነው ብሎ ስለሚያምን የእርሱን (የንጉሠ ነገሥቱን) ትዕዛዝ ያለአንዳችም ሰበብ ወይም ማመካኘት በደስታ ይቀበላል።>> ብለው ያስረዱንን ስርዓት ለዚህ ማዕርግ የበቃ ሰው የቱን ያህል ሥልጣን እንደነበረውና ዝንባሌው የራሱን ሥልጣን የማዳበርም ከሆነ ይሀንን ዓይነት መሠረት ይዞ የዝንባሌውን ዓላማ ስኬታማ ማድረግ እንዴት ቀላል እንደሆነ ይገነዘቧል።
 
በ[[1935|፲፱፻፴፭]] ዓ/ም ፣ ድል በተገኘ በሁለት ዓመቱ፣ ንጉሠ ነገሥቱ “የመንግሥታችችን ሚኒስቴሮች ሥልጣንና ግዴታዎች ለማብራራት” በሚል ዐዋጅ በራሳቸው ሰብሳቢነት የሚመራ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት እና “ቃለ መሐላ” የሰጡ ሚኒስቴሮች መሾማቸውን ሲይስታውቁ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት በፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ እንደሚመራና ምክር ቤቱም በኒሁ ሰው ‘ቁጥጥር’ ስር እንደሚሆን ታወጀ። እኒህ ሚኒስቴር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ውስጥ “ከማናቸውም ባለሥልጣን ጋር በቀጥታ የመገናኘት ሥልጣን” እንደተሰጣቸው ዐዋጁ ለጥቆ አስታወቀ። እንግዲህ በዚህ አዋጅ መሠረት ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ በንጉሠ ነገሥቱ ፍላጎት እና ዐዋጅ የዘውዱን የበላይነት ለማስከበር ሙሉ ሥልጣን ‘እንደራሴ’ መሆናቸው ተረጋግጧል። በሌላ መልክ ሲተረጎም፤ ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ መስቀልዮሐንስ በንጉሠ ነገሥቱ እውቀትም ይሁን ፍላጎት ‘በማስመሰል’ም ይሁን በትክክል የንጉሠ ነገሥት መንግሥቱን ዓላማ በማራመድ ኢትዮጵያን ለማልማት፤ በዘመናዊ መንገድ ለመምራት፤ ‘ለመፍለጥ ለመቁረጥ’፤ የራሳቸውን ባለሟሎች እና ወገኖች በማንኛውም ረገድ ለማዳበር፤ የራሳቸውን የሥልጣን መሠረት ለማስፋፍትም ሆነ የዝዘውድ ስርዓቱን ዘላለማዊ ለማድረግ ልዩና ቁልፋዊ ቦታ እንደነበራቸው እንገነዘባለን።
 
ምስጢራዊና የሥልጣን አያያዝ፣ አጠቃቀም እና ‘ከመለኮት የተሠጠ’ መብታቸውን ከማንም ጋር መሻማት የማይፈልጉትስ ንጉሠ ነገሥት እንደዚህ ዓይነት ዐዋጅ ሲያስተላልፉ፣ ምን አስበው ኖሯል? በጊዜው አገራችንን ከፋሽሽት ጣልያን ለማላቀቅ አባቶቻችን እና እናቶቻችን የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍ ገብተው የነበሩት እንግሊዞች፤ ከድል በኋላ ኢትዮጵያን ቢያንስ በሥራቸው እንደቅኝ ግዛት ለማስተዳደር፤ ይሄ ባይሳካላቸው ደግሞ ሕዝቦቿንና ግዛቷን ከፋፍለው ለመበተን የሚጥሩበት ጊዜ ነበር። ታዲያ ለንጉሠ ነገሥቱ የዚህ አዋጅ መነሻ ምናልባት እንግሊዞች በዓላማቸው የቀናቸው እንደሆነ የሚያሳብቡበት (scape-goat) የዋህ ሰው ማዘጋጀታቸው ኖሯል?
3,107

edits