ከ«ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

no edit summary
==የወጣትነት ዘመናት==
 
ፀሐፌፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ [[ቡልጋ]] አውራጃ ውስጥ መስኖ ዘንባባ በሚባል ሥፍራ በ[[1893|፲፰፻፺፫]] ዓ/ም ከቤተ ክህነት ወገን ተወልደው በዘመኑ ስርዓት የግዕዝ እና አማርኛ ትምሕርታቸውን በዚያው በቤተ ክህነት አጠናቀቁ። ከዚያ ቀጥሎ መቼ፣ እንዴትና ለምን ለሚሉት ጥያቄዎች መረጃ ባይገኝም ሆኔም ቀሬ በ[[ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ]] ዘመን መሆኑ ነው፣ አዲስ አበባ ይመጡና በዳግማዊ ምኒልክ ትምሕርት ቤት [[ፈረንሳይኛ]] ቋንቋ አጥንተዋል። በዚህም የቋንቋ ዕውቀት በአስተርጓሚነት ሲያገለግሉ ቆይተው ኢትዮጵያ የዓለም መንግሥታት ማኅበር አባል ስትሆን በ [[1918|፲፱፻፲፰]] ዓ/ም ወደ ማኅበሩ ፅሕፈት ቤት [[ጀኒቫ|ዠኔቭ]] ይላካሉ።
 
ከዠኔቭ ሲመለሱ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ [[ጣልያን]]፣ [[ቤልጅግ]] እና [[ጀርመን]] ክፍል ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ በ[[1923|፲፱፻፳፫]] ዓ/ም በዚያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲሬክቶርነት ማዕርግ ለሦስት ዓመት አገልግለዋል። <ref> Gebissa, Ezekiel (translation) : “My Life & Ethiopia’s Progress, vol two (1999) pg 16</ref> በ[[1926|፲፱፻፳፮]] ዓ/ም በፅሕፈት ሚኒስቴር ጠቅላይ ዲረክቶር ተብለው ለጥቀውም የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ ሆነው እስከ ጠላት ወረራ ድረስ ሲያገለግሉ ቆዩ። ከንጉሠ ነገሥቱም ጋር የቅርብ ግንኙነታቸውና ወደፊት የሚይዙትም የ’ፈላጭ ቆራጭነት’ ሥልጣን የተመሠረተው በዚህ ጊዜ እንደሆነ ይገመታል።
==የጠላት ወረራና ያስከተለው ስደት==
 
የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ አቶ ወልደ ጊዮርጊስ [[ፋሽሽት ኢጣልያ]] አገራችንን በወረረ ጊዜ ክንጉሠ ነገሥቱ ሳይለዩ፣ በማይጨው ዘመቻ ከአዲስ አበባ ወደደሴ አብረው [[ኅዳር 18|ኅዳር ፲፰]] ቀን [[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ/ም ይጓዛሉ ።<ref> Mockler, Anthony: “Haile Selassie’s War” (2003) pg 73</ref> በኋላም [[ግንቦት]] ወር [[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ/ም በ[[ጂቡቲ]] እና በ[[ኢየሩሳሌም]] በኩል አድርገው ከ[[ሐይፋ]] ወደብ እስከ [[ጅብራልታ]] በ[[እንግሊዝ]] የጦር መርከብ፣ ከጅብራልታር እስከ [[ሳውዝሃምፕቶን]] የእንግሊዝ ወደብ በመንገደኛ መርከብ ተጉዘው የአምስት ዓመት የስደታቸውን ዘመን አብረው ተሳትፈዋል።
 
በስደት ዘመን ንጉሠ ነገሥቱ ከቤተሰባቸው ጋር በ[[ባዝ]] ከተማ “ፌየርፊልድ ሃውስ” የስደት ዘመን እንዳሳለፉ ብዙ ተጽፏል። ከቤተ ሰቡም ጋር አብረው የነበሩ (ሠራተኞች፣ አገልጋዮች፣ መነኮሳት) ሌሎች ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንደነበሩ ‘ሉትዝ ሄበር’ (Lutz Haber) “ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በባዝ ከ 1928 – 1932 ዓ.ም” (The Emperor Haile Sellasie I in Bath 1936 – 1940) በሚል ጽሑፉ በሰፊው አስፍሮታል።
በዚያ የስደት ዘመን ግን ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ የት እንደኖሩ መረጃ ማግኘት ባይቻልም የንጉሠ ነገሥቱ የግል ጸሐፊ ስለነበሩ እምብዛም እንድማይርቋቸው ይገመታል። ሆኔም ቀሬ በታኅሣሥ [[1929|፲፱፻፳፱]] ዓ/ም የፈረንጆች ገና ዕለት ንጉሠ ነገሥቱ በ[[ቢቢሲ]] ራዲዮ ለ[[አሜሪካ]]ውያን ደጋፊዎቻቸው መልዕክት ሲያስተላልፉ፣ በስደት የዲፕሎማሲ ትግል ሲያካሂዱና ከዓለም መንግሥታት ማኅበር ጋር ‘የአእምሯዊ ግብግብ’ በገጠሙበት ጊዜ አጠገባቸው ሆነው ከሚያማክሯቸው ሰዎች አንዱ አቶ ወልደ ጊዮርጊስ እንደነበሩ ንጉሥ ነገሥቱ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ - ፪ኛ መጽሐፍ” ላይ ጠቅሰውታል።
 
==ከድል እስከ ግዞት==
 
<<የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሥልጣን በግዛቱ ውስጥ ያልተወሰነ ነው። ሥልጣኑ ሃይማኖታዊም ሆነ ሥጋዊ ጉዳዮችን ያጠቃልላል። በሥልጣኑ ይሾማል፣ ይሽራል መውሰድም፣ መስጠትም፤ ማሠርም፣ መፍታትም፤ መግደልም፣ መስቀልም ይችላል። ትንሹም ትልቁም ንጉሠ ነገሥቱ የእግዚአብሔር ተወካይ ነው ብሎ ስለሚያምን የእርሱን ትዕዛዝ ያለአንዳችም ሰበብ ወይም ማመካኘት በደስታ ይቀበላል።>> “ዝክረ ነገር” ከ [[ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል (ብላቴን ጌታ)| ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል]] <ref> Markakis, pg 252</ref>
የስድሳ ስድስቱ አብዮት ኃይለ ሥላሴን ከሥልጣን ከማውርደኡ ከጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ ለሕክምና ወደ እንግሊዝ አገር ይሄዱና ሁለተኛውንና የመጨረሻውን የስደት ዘመን ጀምረው በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው እዚያው እንግሊዝ አገር አርፈው ተቀበሩ።
 
==ሥነ ጽሑፍ==
 
ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ለአማርኛ ቋንቋ ካበረከቷቸው ድርሰቶች
 
== ከድርሰቶቻቸው ==
 
===ከአምስት መንገዶች ([[1954|፲፱፻፶፬]] ዓ/ም)===
 
የሰው አሳብና የውሻ ጅራት ዘወትር ወደ ላይ ነው፡፡ ነገር ግን ውሻ በትር ሲመዘዝበት ጅራቱን እንዲሸጉብ፤ ሰውም ላይ ላዩን እላለሁ ሲል አንድ ዓይነት አደጋ ሲወድቅበት ጭብጥ እንኳ አይሞላም፤ ከአዳም መወለዱን የሚያምን ሁሉ ይህን ሊክድ አይችልም፡፡
 
 
===ሁሉም ከመሬት ተፈጥሮአል===
 
ማንጠልጠያ የሌለው ከበሮ ከተጋደመበት ሲጐስሙት ድምፁን ማሰማቱ አይቀርም፡፡ ሃይማኖት የሌለው ሰው ግን ምን ድምፅ አለው፡፡"" ቢኖረውስ ምን ፍሬ ነገር ሊያሰማበት ነው ቢሆንም ከሃይማኖተ ውጭ አፍ እላፊ አላደርግም፡፡ "ሽንብራ ዱቤ አይገኝም በዱቤ" እንደ ተባለው የሃይማኖት ፍሬ ያለሃይማኖት በዱቤ ያለመገኘቱ እየታወቀ እንዴት ሰው ያለ ሃይማኖት ይኖራል፡፡ ይህማ እንደ እንስሶች መሆን አይደለምን፤ እንዳያውም እንስሳት ሃይማኖት ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም ምን ቸገራቸው፡፡ ቢጠመዱም፤ ቢታረዱም፤ ቢገረፉም፤ ቢገፊፉም፤ ጣጣቸው የሚያልቀው በዚሁ በታችኛው ዓለም ስለሆነ ከሞት በኋላ ነፃ ናቸው፡፡
ከዚህም ላይ ልብ የሚመታና በስሜት ላይ መገረምን የሚጥል ቃል በማግኘቴ ሲከነክነኝ ይኖራል፡፡ እሱ እኮ ነገረኛ ነው፡፡ ተጠራጥሮ ያጠራጥራል፡፡ "የሰው ልጆችና የእንስሳ እጣ ነው፡፡ ድርሻቸውም የተስተካከለ ነው፡፡ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከንቱ ነውና፡፡ ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሔዳል፡፡ ሁሉም ከመሬት ተፈጥሮአል፡፡ ሁሉም ወደ መሬት ይመለሳል፡፡ የሰው ልጆች ነፍስ ወደ ላይ እንድትወጣ፤ የእንስሳም ነፍስ ወደ ምድር በታች እንድትወርድ ለይቶ የሚያውቅ ማነው" ይላል፡፡
 
==አባብሎችአባባሎች==
-* ደስ መሰኘትና መከፋት ሲዘዋወሩ ስለሚኖሩ ደስ ያለው እንደሚከፋው፣ የከፋው ደስ እንደሚለው አይጠረጠርም፡፡
 
-* በዕድሜ መሰንበትና ፈተናን ሁሉ አልፎ ወደ ደህና ቀን መድረስ ብዙ ጊዜ መታደልና መክበር ነው፡፡
- ደስ መሰኘትና መከፋት ሲዘዋወሩ ስለሚኖሩ ደስ ያለው እንደሚከፋው፣ የከፋው ደስ እንደሚለው አይጠረጠርም፡፡
-* በእናት ማኅፀን የተፀነሰ ፅንስ ቀኑ ሲደርስ በማኅፀን ታግዶ እንደማይቀር ሥራም በትጋት ከተጀመረ የሠራተኛው አሳብ ከወሰነው ጊዜ አያልፍም፡፡
- በዕድሜ መሰንበትና ፈተናን ሁሉ አልፎ ወደ ደህና ቀን መድረስ ብዙ ጊዜ መታደልና መክበር ነው፡፡
-* ፍልስፍና አድራሻ የለውም፤ ያለ ዕረፍት ሲሄድ የሚኖር የምርመራ አሞራ ከመሆኑም የተነሳ ከሁሉ ይደርሳል፡፡
- በእናት ማኅፀን የተፀነሰ ፅንስ ቀኑ ሲደርስ በማኅፀን ታግዶ እንደማይቀር ሥራም በትጋት ከተጀመረ የሠራተኛው አሳብ ከወሰነው ጊዜ አያልፍም፡፡
-* ማወቅ ወጣም ወረደ ለመደነቅ ብቻ አይደለም፤ ስህተት የሌለበት ሙሉ ሰውን ለመሆንም ነው እንጂ፡፡
- ፍልስፍና አድራሻ የለውም፤ ያለ ዕረፍት ሲሄድ የሚኖር የምርመራ አሞራ ከመሆኑም የተነሳ ከሁሉ ይደርሳል፡፡
-* ሥጋ በመንፈስ እየተንቀሳቀሰ፣ መንፈስ በሥጋ እየተዳበሰ ግዙፍነትንና ረቂቅነትን ለመግለጽ፣ መንፈስ ወደ መንፈሳዊነት፣ ሥጋም ወደ ሥጋዊነት እያዘነበለ፣ በአንድ ሰው አካል ሁለት ኃይል ሲሠራ ይኖራል፡፡
- ማወቅ ወጣም ወረደ ለመደነቅ ብቻ አይደለም፤ ስህተት የሌለበት ሙሉ ሰውን ለመሆንም ነው እንጂ፡፡
- ሥጋ በመንፈስ እየተንቀሳቀሰ፣ መንፈስ በሥጋ እየተዳበሰ ግዙፍነትንና ረቂቅነትን ለመግለጽ፣ መንፈስ ወደ መንፈሳዊነት፣ ሥጋም ወደ ሥጋዊነት እያዘነበለ፣ በአንድ ሰው አካል ሁለት ኃይል ሲሠራ ይኖራል፡፡
(ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ 1935)
 
==ማጣቀሻ==
 
<references/>
 
==ዋቢ ምንጮች==
 
* ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ፣ አንደኛ መጽሐፍ (፲፱፻፳፱) ዓ/ም
* Gaitachew Bekele, "The Emperor’s Clothes" (1993)
6,498

edits