ከ«ሠርፀ ድንግል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 2፦
| ስም = ዓፄ ሠርፀ ድንግል
| ሀገር = ኢትዮጵያ
| ስዕል = GuzaraCastleGuzaraCastle1.jpg
| የስዕል_መግለጫ = በ[[እምፍራዝ]]፣ [[ጎንደር]] በ1571 ዓፄ ሠርፀ ድንግል የገነቡት የጉዛራ ቤተ መንግስት
| ግዛት = ከ1563 እስከ 1597 እ.ኤ.አ.
መስመር፡ 35፦
ከዚያም ባህር ንጉስ [[ይስሐቅ]] በ[[ኦቶማን]] ቱርኮችና በ[[አዳል]] ሰራዊት ታግዞ አመጽ ማስነሳቱ አልቀረም። በዚህ ጊዜ ንጉሱ ወደ [[ትግራይ]] በመዝመት በ1578 ባህረ ነጋሹንና (በአዲ ቆሮ) አባሪ ኦቶማኑን [[ኦዝደሚር ፓሻ]]ንና የአዳል መሪ የነበረውን ሱልጣን [[መሃመድ አራተኛ]] (በተምቤን) ጦርነት አሸንፎ ገደላቸው። በ[[ድባርዋ]] (የድሮው ኤርትራ ዋና ከተማ) የነበሩት ቱርኮችም ያለምንም ተኩስ እጃቸውን ሰጡ። በዚያውም ሰርጸ ድንግል በአክሱም ስርዓተ ተክሊሉን ፈጸመ (ይህ እንግዲህ ከ[[ዘርዓ ያዕቆብ]] በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው)፣ መልአክ ሰገድ የሚለውንም ስም ያገኘው በዚህ ግዜ ነበር። ከ10 አመት በሁዋላ፣ በ1588 ኦቶማን ቱርኮች፣ ከተባረሩበት [[ድባርዋ]] መልሰው ሊቆጣጠሩ ሲሞክሩ በመሸነፋቸው [[አርቂቆ]] ላይ የነበረውን ግዛታቸውን ሰርጸ ድንግል አፈረሰባቸው። በዚህ ምክንያት የቱርኩ መሪ [[ፓሻ]] በወርቅ ያጌጠ ፈረስ እስከ ሳዱላው በመላክ ከንጉሱ ዘንድ ሰላም እንደሚሻ አስታወቀ። <ref>Hubert Jules Deschamps,(sous la direction). ''Histoire générale de l'Afrique noire de Madagascar et de ses archipels'' Tome I : Des origines à 1800. Page 410-411 P.U.F Paris (1970); </ref>
 
[[ስዕል:GuzaraCastle1GuzaraCastle.jpg|left|thumb|300px|ቱርኮችን በ1569 ድል ካድረጉ በኋላ ለመታሰቢያነት በ[[እምፍራዝ]]፣ [[ጎንደር]] በ1571 ዓፄ ሠርፀ ድንግል የገነቡት የጉዛራ ቤተ መንግስት]]
==ሌሎች ዘመቻወች እና ሰላም ==
ሰርጸ ድንግል የኖረበት ዘመን ከ[[ግራኝ አህመድ]] ወረራ ጥቂት ዘመን አሳልፎ ስለነበር የህዝቦች ፍልሰት በዚሁ ዘመን ይታይ ነበር። የኦሮሞን ወደ ሰሜን ወረራ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋፈጠ ንጉስ ይሄው ሰርጸ ድንግል ነው። በዚሁ ዘመን የኦሮሞወች ጥንካሬ ከማየሉ የተነሳ [[ኑር ኢብን ሙጃሂድ]] የተሰኘውን የግራኝን ምትክ በመግደል [[ሐረር]]ን ወረው ነበር። ቀጥሎም ወደሰሜን በመዝመት ሰርጸ ድንግል በነገሰ በ10ኛው አመት [[ዝዋይ ሃይቅ]] አካባቢ ከንጉሱ ሰራዊት ጋር ተጋጭተው ተሸነፉ። ከዚህ በኋላ ንጉሱ በኦሮሞወች ቡድኖች ላይ በ1578 እና በ1588 ዘምቷል።