ከ«ኤንመርካር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 2፦
 
የኤንመርካር ስም በሌላ የሱመር ጽሑፍ ደግሞ ተገኝቷል። ''[[ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ]]'' በተባለው ተረት እሱ የኡቱ ልጅ ይባላል። (ኡቱ በሱመር እምነት የ[[ጸሓይ]] አምላክ ነበር።) ይህ ተረት የሰው ልጅ ልሳናት መደባለቁን ይናገራል። ኡሩክን ከመመስረቱ በላይ ታላቅ መስጊድ በ[[ኤሪዱ]]ም እንዳሰራ ይተረታል።
 
በተጨማሪ በዚሁ ጽሑፍ ኤንመርካር የዙሪያው አገሮች ልዩ ልዩ ልሳናት እንደገና አንድ እንዲሆኑ ይጸልያል። እነዚህ አገራት [[ሹቡር]]፣ [[ሐማዚ]]፣ [[ሱመር]]፣ ኡሪ-ኪ (የ[[አካድ]] ዙርያ) እና [[አሞራውያን|የማርቱ አገር]] ናቸው።
 
[[ዴቪድ ሮኅል]] የሚባል አንድ የ[[ታሪክ]] ሊቅ የኤንመርካርና የ[[ናምሩድ]] ተመሳሳይነት አመልክቷል። «-ካር» የሚለው ክፍለ-ቃል በሱመር ቋንቋ ማለት «አዳኝ» ነው። ኡሩክ ከተማ የተመሠረተ በኤንመር-ካር ነበር ሲባል፣ ደግሞ ናምሩድ፣ አዳኝ፣ በ[[ኦሪት ዘፍጥረት]] ምእራፍ 10 ዘንድ ኦሬክን ሰራ። በሌላ ትውፊቶች ዘንድ ይህ ናምሩድ [[የባቢሎን ግንብ]] መሪ የሆነ ነበር። በተጨማሪም አቶ ሮህል የኤሪዱ መጀመርያ ስም «ባቤል» እንደ ነበር ያምናል፤ እዚያም የሚገኘው የግንብ ፍረስራሽ የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ መሆኑን ገመተ።
 
ሌላ ''ሉጋልባንዳና አንዙድ ወፍ'' የተባለ ጽሑፍ እንደሚል፣ ኤንመርካር 50 አመት ከገዙ በኋላ፣ የማርቱ ሕዝብ (አሞራውያን) በሱመርና በአካድ ሁሉ ተነሥተው ኡሩክን ለመጠብቅ ግድግዳ መስራት ነበረበት።
 
በሱመር ነገሥታት ዝርዝርና እንዲሁም ''ሉጋልባንዳ በተራራ ዋሾ'' በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ የኤንመርካር ሠራዊት አለቃ [[ሉጋልባንዳ]] ወደ ኡሩክ ዙፋን ተከተለው። ይህም ሉጋልባንዳ የ[[ጊልጋመሽ]] አባት ነበረ።