ከ«የአቅጣጫ ቁጥር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''የአቅጣጫ ቁጥር''' በእንግሊዝኛ Complex Number የሚባል ሲሆን የእንግሊዝኛው ስሙ ግን ስህተት ወይም የሚያ...»
(No difference)

እትም በ13:15, 20 ጁን 2010

የአቅጣጫ ቁጥር በእንግሊዝኛ Complex Number የሚባል ሲሆን የእንግሊዝኛው ስሙ ግን ስህተት ወይም የሚያምታታ ነው። የአቅጣጫ ቁጥሮች ሲጻፉ ባጠቃላይ መልኩ a+jb ወይም a+ib በሚል ሲገለጹ፣ a ና b የውን ቁጥር ሲሆኑ፣ i (በሂሳብ) ወይም j (ኤሌክትሪክ ምህንድስና ) ደግሞ ንጹህ የአቅጣጫ ቁጥር ናቸው።

i ወይም j, ንጹህ የአቅጣጫ ቁጥር የተባሉበት ምክንያት ይሄ ነው፦

አድማሳዊ መስመር x ላይ ያለን ቁጥር በ1 ብናበዛው እዚያው መስመር ላይ፣ ያኑ ቁጥር እናገኛለን። ነገር ግን በ -1 ብናበዛ ያ ቁጥር በ180o ዲግሪ ይገለበጥና ተቃራኒውን ይሰጠናል። በ180o ለመገልበጥ ሁለት ጊዜ በ90o ዲግሪ መገልበጥ ስለሚያስፈልግ፣ ሁለት ጊዜ ተባዝቶ -1 የሚስጠን ስለሆነ፣ እንግዲይ ይህ ቁጥር ንጹህ የአቅጣጫ ቁጥር ነው ማለት ነው።