ከ«ኒኑስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
Content deleted Content added
ጥ ሎሌ መጨመር: en:Ninus |
No edit summary |
||
መስመር፡ 2፦
'''ኒኑስ''' በጥንታዊ የ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ የ[[ነነዌ]] መስራችና የ[[አሦር]] ንጉስ ነበረ። ለዘመናዊ ሥነ ቅርስ የታወቀ አንድ ግለሰብ አይመስልም፤ ዳሩ ግን የአያሌ ታሪካዊ ወይም አፈ ታሪካዊ ግለሰቦች ትዝታ በአንድ ስም በግሪኮች በኋለኛ ዘመን እንደ ተዘከረ አሁን ይታስባል።
የንጉሥ ኒኑስና ሚስቱ ንግሥት [[ሴሜራሚስ]] ስሞች በጽሁፍ መጀመርያ የተገኘው [[ክቴስያስ ዘክኒዱስ]] (400 ዓክልበ. ገዳማ) በጻፈው በ[[ፋርስ]] አገር ታሪክ ነው። ክቴስያስ ለ[[2 አርጤክስስ]] (2 አርታሕሻጽታ) የመንግሥት ሀኪም ሆኖ የፋርስ ነገሥታት ታሪካዊ መዝገቦች አንብቤያለሁ ብሎ አሳመነ።<ref>''"Like a Bird in a Cage": The Invasion of Sennacherib'', Lester L. Grabbe (2003), p. 121-122</ref> ከዚህ በኋላ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]]
ኒኑስ የ[[ቤሉስ]] ወይም [[ቤል]] ልጅ ተባለ፤ ይህም ምናልባት በሴማዊ ቋንቋ ሥር «ባል» (ጌታ) የመሰለ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። በ[[ካስቶር ዘሮድስ]] ዘንድ ኒኑስ ለ52 ዓመታት ነገሰ፤ ክቴስያስም እንዳለው መጀመርያው ዓመተ መንግሥቱ 2198 ዓክልበ. ነበረ። በ17 አመታት ውስጥ ኒኑስ በ[[አረቢያ]] ንጉስ አርያዎስ እርዳታ ምዕራብ [[እስያ]]ን በሙሉ እንዳሸነፈ ተብሏል። ከዚህ ቀጥሎ የ[[አርመን]] ንጉስ ባርዛኔስን (ይቅርታ የሰጠው) እና የ[[ሜዶን]] ንጉስ ፋርኖስን (በስቅለት ይሙት በቃ የሰጠው) ድል በማድረግ የአለም መጀመርያ ንጉሠ ነገስት እንደ ሆነ ተብሏል።
|