ከ«ኒኑስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 2፦
'''ኒኑስ''' በጥንታዊ የ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ የ[[ነነዌ]] መስራችና የ[[አሦር]] ንጉስ ነበረ። ለዘመናዊ ሥነ ቅርስ የታወቀ አንድ ግለሰብ አይመስልም፤ ዳሩ ግን የአያሌ ታሪካዊ ወይም አፈ ታሪካዊ ግለሰቦች ትዝታ በአንድ ስም በግሪኮች በኋለኛ ዘመን እንደ ተዘከረ አሁን ይታስባል።
 
የንጉሥ ኒኑስና ሚስቱ ንግሥት [[ሴሜራሚስ]] ስሞች በጽሁፍ መጀመርያ የተገኘው [[ክቴስያስ ዘክኒዱስ]] (400 ዓክልበ. ገዳማ) በጻፈው በ[[ፋርስ]] አገር ታሪክ ነው። ክቴስያስ ለ[[2 አርጤክስስ]] (2 አርታሕሻጽታ) የመንግሥት ሀኪም ሆኖ የፋርስ ነገሥታት ታሪካዊ መዝገቦች አንብቤያለሁ ብሎ አሳመነ።<ref>''"Like a Bird in a Cage": The Invasion of Sennacherib'', Lester L. Grabbe (2003), p. 121-122</ref> ከዚህ በኋላ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] የክቴስያስ ወሬ አስፋፋ። የአለም ታሪክ ሊቃውንት እስከ [[1880ዎቹ]] ድረስ የኒኑስ ታሪክ ዕውነት መሆኑን ይቈጠሩት ነበር። በዚያን ጊዜ [[የኩኔይፎርም ጽሕፈት]] ፍች ስለ ተፈታ፣ በ[[ሜስፖጦምያ]]ና በነነዌ ብዙ ቅርሶችም በመገኘታቸው፣ የአሦር ትክክለኛ ታሪክ ዕውቀት ተጨመረልን።
 
ኒኑስ የ[[ቤሉስ]] ወይም [[ቤል]] ልጅ ተባለ፤ ይህም ምናልባት በሴማዊ ቋንቋ ሥር «ባል» (ጌታ) የመሰለ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። በ[[ካስቶር ዘሮድስ]] ዘንድ ኒኑስ ለ52 ዓመታት ነገሰ፤ ክቴስያስም እንዳለው መጀመርያው ዓመተ መንግሥቱ 2198 ዓክልበ. ነበረ። በ17 አመታት ውስጥ ኒኑስ በ[[አረቢያ]] ንጉስ አርያዎስ እርዳታ ምዕራብ [[እስያ]]ን በሙሉ እንዳሸነፈ ተብሏል። ከዚህ ቀጥሎ የ[[አርመን]] ንጉስ ባርዛኔስን (ይቅርታ የሰጠው) እና የ[[ሜዶን]] ንጉስ ፋርኖስን (በስቅለት ይሙት በቃ የሰጠው) ድል በማድረግ የአለም መጀመርያ ንጉሠ ነገስት እንደ ሆነ ተብሏል።