ከ«ኒኑስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
translation of English article - C.S.
 
No edit summary
መስመር፡ 2፦
'''ኒኑስ''' በጥንታዊ የ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ የ[[ነነዌ]] መስራችና የ[[አሦር]] ንጉስ ነበረ። ለዘመናዊ ሥነ ቅርስ የታወቀ አንድ ግለሰብ አይመስልም፤ ዳሩ ግን የአያሌ ታሪካዊ ወይም አፈ ታሪካዊ ግለሰቦች ትዝታ በአንድ ስም በግሪኮች በኋለኛ ዘመን እንደ ተዘከረ አሁን ይታስባል።
 
የንጉሥ ኒኑስና ሚስቱ ንግሥት [[ሴሜራሚስ]] በጽሁፍ መጀመርያ የተገኘው [[ክቴስያስ ዘክኒዱስ]] (400 ዓክልበ. ገዳማ) በጻፈው በፋርስበ[[ፋርስ]] አገር ታሪክ ነው። ክቴስያስ ለ[[2 አርጤክስስ]] (2 አርታሕሻጽታ) የመንግሥት ሀኪም ሆኖ የፋርስ ነገሥታት ታሪካዊ መዝገቦች አንብቤያለሁ ብሎ አሳመነ።<ref>''"Like a Bird in a Cage": The Invasion of Sennacherib'', Lester L. Grabbe (2003), p. 121-122</ref> ከዚህ በኋላ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] የክቴስያስ ወሬ አስፋፋ። የአለም ታሪክ ሊቃውንት እስከ [[1880ዎቹ]] ድረስ የኒኑስ ታሪክ ዕውነት መሆኑን ይቈጠሩት ነበር። በዚያን ጊዜ [[የኩኔይፎርም ጽሕፈት]] ፍች ስለ ተፈታ፣ በ[[ሜስፖጦምያ]]ና በነነዌ ብዙ ቅርሶችም በመገኘታቸው፣ የአሦር ትክክለኛ ታሪክ ዕውቀት ተጨመረልን።
 
ኒኑስ የ[[ቤሉስ]] ወይም [[ቤል]] ልጅ ተባለ፤ ይህም ምናልባት በሴማዊ ቋንቋ ሥር «ባል» (ጌታ) የመሰለ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። በ[[ካስቶር ዘሮድስ]] ዘንድ ለ52 ዓመታት ነገሰ፤ ክቴስያስም እንዳለው መጀመርያው ዓመተ መንግሥታቸው 2198 ዓክልበ. ነበረ። በ17 አመት ውስጥ በ[[አረቢያ] ንጉስ አርያዎስ እርዳታ ምዕራብ [[እስያ]]ን በሙሉ እንዳሸነፈ ተብሏል። ከዚህ ቀጥሎ የ[[አርመን]] ንጉስ ባርዛኔስን (ይቅርታ የሰጠው) እና የ[[ሜዶን]] ንጉስ ፋርኖስን (በስቅለት ይሙት በቃ የሰጠው) ድል በማድረግ የአለም መጀመርያ ንጉሠ ነገስት እንደ ሆነ ተብሏል።
 
[[File:Ninus.png|thumb|left|300px|የኒኑስ መንግሥት ስፋት በዲዮዶሮስ ዘንድ]]]]
 
ግሪኮቹ እንደ ተረኩት፣ ይህ ኒኑስ በዙርያው ያሉትን እስያዊ አገሮች ከ[[ሕንድ]]ና ከ[[ባክትርያና]] በስተቀር በሙሉ አሸነፋቸው። ከዚያ ወዲያ ኒኑስ በ2 ሚሊዮን ወታደሮች ሠራዊት በባክትርያና ንጉሥ በኦክስያርቴስ ላይ ወረራ ጀመረ። አገሩ ሁሉ ቢወድቅም ዋና ከተማው [[ባክትራ]] ግን አልወደቀምና ሠራዊቱ ከበቡት። ባክትራን ሲከብቡት ኒኑስ የመኮነኑ [[ኦኔስ]] ሚስት ሴሜራሚስ አገኛትና ከባልዋ እንደ ራሱ ሚስት ያዛት። ልጃቸው የኒኑስ ተከታይ [[ኒንያስ]] ሆነ።