ከ«መጽሐፈ ኩፋሌ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''መጽሐፈ ኩፋሌ''' በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በ[[ዲዩትሮ...»
(No difference)

እትም በ15:07, 12 ሜይ 2010

መጽሐፈ ኩፋሌኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍት አንዱ ነው። በሌሎቹ አብያታ ክርስትያናት ግን ዛሬ የማይቀበል መጽሐፍ ወይም ሲውዴፒግራፋ ይባላል። ነገር ግን ለቀድሞው የቤተ ክርስቲያን አበው ታውቆ የጥቅስ ምንጭ ሆነላቸው። የመጽሐፉ ግሪክ ትርጉም የሚታወቀው ከቅዱስ ኤፒፋንዮስ ጥቅሶች ባቻ ሳይሆን እንዲሁም በዩስቲን ሰማዕት፣ በኦሪጄን፣ በዲዮዶሮስ ዘአንጥያክያ፣ በኢሲዶር ዘሰቪላ፣ በአሲዶር ዘእስክንድርያ፣ በዩቲክዮስ (አቡነ እስክንድርያ)፣ በ[[ዮሐንስ ዘማላላ፣ በጊዮርጊስ ሱንኬሎስና በቄድሬኖስ ጥቅሶች በከፊል ይታወቃል።

ሆኖም መጽሐፉ በአይሁድ ሳንሄድሪን1ኛው ክፍለ ዘመን እንደ ቅዱሳን መጻሕፍት አልተቀበለም ነበር። አንዳንድ ክፍል በቁምራን ዋሾ በ1939 ዓ.ም. እስከተገኘ ድረስ፣ የመጽሐፉ ዕብራይስጥ ትርጉም በሙሉ ጠፍቶ ነበር። ስለዚሁ ሁኔታ (የዕብራይስጥ ትርጉም በማጣት) መጽሐፉ በኋላ ዘመን በሮማ ቤተ ክርስቲያን አለቆች አልተቀበለም። ሆኖም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዘንድ መጽሐፉ በግዕዝ ስለ ተገኘ እስከ ዛሬ ድረስ ቅዱስ ተብሎ ተከብሯል።

መጽሐፉ እንደሚለው መላእክት የዓለሙን ታሪክ ከፍጥረት ጀምሮ እስከ ኦሪት ዘጸአት ድረስ ለሙሴደብረ ሲና ይተርካሉ። ዘመናት በኢዮቤልዩ ወይም በ49 ዓመታት ይከፋፈላሉ። ኢያንዳንዱ ኦዮቤልዩ 7 ሱባዔ ወይም የዓመት ሳምንት (7 አመት) ነው። ከማየ አይህ አስቀድሞ ደቂቃ ሴት ከእግዚአብሔር አምጸው ወደ ቃየን ልጆች እንደ ሐዱና እንደ ከለሱ ይላል። ክልስ ልጆቻቸውም ክፉ ረጃጅሞች (ናፊሊም) ሆነው በማየ አይህ ጠፉ። ከዚህ በኋላ የኖህን ልጆች አሳቱ። ጣኦት ሠሩ፣ መንግሥት አጸኑ፣ የኖህ ልጆች ምድርን ሁሉ ያካፈላሉ፣ የባቢሎን ግንብ ከወደቀ ቀጥሎ ወደ ርስቶቻቸው ተበተኑ። መላእክትም ለአብርሃም ቅዱስ ቋንቋን ያሳውቁት።

ከተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውጭ እንደ «ሲውደፒግራፋ» በመቆጠሩ አንዳንድ ሊቃውንት በ150 ዓክልበ. ገደማ እንደ ተሠራ ይገምታሉ። ለዚሁ አስተሳሰብ ግን ምንም ማስረጃ አልተገኘም።

የውጭ መያያዣዎች