ከ«ሊያ ከበደ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 12፦
ሊያ በተመሳሳይ በ[[ጣልያን]]፣ [[ጃፓን]]፣ [[አሜሪካ]]፣ [[ስፔን]]፣ [[ፈረንሣይ]] Vogue መፅሔት እትሞች ላይ እና በTime's Style & Design ላይ የሽፋን ቦታን በተለያዩ ጊዜያት አግኝታለች። እ.አ.አ. በ2003 ለEstée Lauder ኮስሞቲክስ በ57 አመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ተወካይ በመሆን የ3 ሚሊዮን [[ዶላር]] ስምምነት ፈርማለች።
 
በፎቶ ትዕይንቶች ላይ ጎልተው ከሚታዩ ጥቂት የ[[አፍሪካ]] ሞዴሎች አንዷም ናት። በነዚህም ታዋቂነቶቿ እና በመልካም ተግባሯ እ.አ.አ. በ2005 የአለም የጤና ድርጅት በእናቶች፣ አዲስ በሚወለዱ ህፃናት እና የሕፃናት ጤና ጥበቃ አምባሳደር ሆናለች። እ.አ.አ. በ2005 American Vogue መፅሔት ይህንኑ ሠብዓዊ ተግባሯን በመጥቀስ እና የፊት ገፅ ላይ ምስሏን በማውጣት ከጥቂት ጥቁር ሞዴሎች ተርታ እንድትሰለፍ አስችሏታል። በአንድ ወቅት ሊያ ስለአፍሪካ ስትናገር "ይህንን ስሜት የፈጠረብኝ አፍሪካ ውስጥ ተወልጄ ማደጌ ነው። በድኅነት ተከቦ እየኖሩ ስለድኅነት አለማሰብ ፈፅሞ የማይቻል ነገር ነው። ልጅህን በምትወልድበት በዚያችው ደቂቃ ነው ለልጅህ የተሻለች ዓለም ትተህ ማለፍ እንዳለብህ ማሰብ የምትጀምረው" ብላ ነበር።
 
[[ስዕል:398px-Liya_Kebede2.jpg|ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደ በእ.አ.አ. 2008 የCarolina Herrera የፋሽን ቴይንት ላይ|thumbnail|200px|left]] በጁሌይ 2007 እ.አ.አ. ላይ [[ፎርብስ]] 2.5 ሚሊዮን [[ዶላር]] ገቢ በማግኘት ከዓለማችን 15 ከፍተኛ ተከፋይ ሡፐር ሞዴሎች 12ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
መስመር፡ 23፦
 
ሊያ ከበደ የhedge fund ማናጀር ከሆነው ባለቤቷ ኬሲ ከበደ ጋር በትዳር የተሳሰሩት እ.አ.አ. በ2000 ሲሆን የሁለት ልጆች እናት ናት። ስሁል የሚባለው ልጇ በእ.አ.አ. በ2001 የተወለደ ሲሆን ሬይ የተባለችው ልጇ ደግሞ እ.አ.አ. በ2005 ነው የተወለደችው። እ.አ.አ. በ2007 ቤተሠባቸው በ[[ኒው ዮርክ]] ከተማ መኖር ጀመረ።
 
 
 
{{መዋቅር}}