ከ«ሊያ ከበደ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «[[ስዕል:487px-Liya_Kebede_at_the_2008_Tribeca_Film_Festival.JPG|ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደ በእ.አ.አ. 2008 የትራይቤካ የፊልም ፌስ...»
 
No edit summary
መስመር፡ 4፦
==የህይወት ታሪክ==
 
ሊያ ከበደ የተወለደችው በ[[ኢትዮጵያ]] ውስጥ በ[[ዋና ከተማ]]ዋ [[አዲስ አበባ]] እ.አ.አ. ጃንዌሪ 3፣ 1978 ነው። አንድ የፊልም ዳይሬክተር ነበር Lycee Guebre Mariamን በመታደም ላይ ሳለች ያያት እናም ከ[[ፈረንሣይ]] የሞዴል ባለሙያ ጋር ያስተዋወቃት። ጥናቷን ካጠናቀቀች በኋላ ነበር ከ[[ፐርሺያ]] ኤጀንሲ ጋር ለመስራት ወደ [[ፈረንሣይ]] ያቀናችው። በኋላም ወደ [[ኒው ዮርክ]] ከተማ ተዛወረች። እናም የውጭው አለም የፋሽን መድረክ ከሀገርኛው ጋር ፍፁም የተለያየ መሆኑን ተገነዘበች።
 
==የሞዴልነት ሥራ==
 
ሊያ ትልቁ ወደሆነው የህይወቷ ምዕራፍ የተሸጋገረችው [[ቶም ፎርድ]] የተባለ ግለሠብ Gucci ለተባለ የክረምት ፋሽን ትርኢት እ.አ.አ. 2000 ላይ እንድትካፈል ከጠየቃት በኋላ ነበር። የሊያ እውቅና እጅጉን የጨመረው በእ.አ.አ. 2002 Paris Vogue መፅሔት እትም ላይ የውጭ ሽፋን ከሠጣት እና ሙሉ ይዘቱን ማለት ይቻላል ስለ እርስዋ ካደረገ በኋላ ነበር።
 
ሊያ በተመሳሳይ በ[[ጣልያን]]፣ [[ጃፓን]]፣ [[አሜሪካ]]፣ [[ስፔን]]፣ [[ፈረንሣይ]] Vogue መፅሔት እትሞች ላይ እና በTime's Style & Design ላይ የሽፋን ቦታን በተለያዩ ጊዜያት አግኝታለች። እ.አ.አ. በ2003 ለEstée Lauder ኮስሞቲክስ በ57 አመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ተወካይ በመሆን የ3 ሚሊዮን [[ዶላር]] ስምምነት ፈርማለች።
 
በፎቶ ትዕይንቶች ላይ ጎልተው ከሚታዩ ጥቂት የ[[አፍሪካ]] ሞዴሎች አንዷም ናት። በነዚህም ታዋቂነቶቿ እና በመልካም ተግባሯ እ.አ.አ. በ2005 የአለም የጤና ድርጅት በእናቶች፣ አዲስ በሚወለዱ ህፃናት እና የሕፃናት ጤና ጥበቃ አምባሳደር ሆናለች።
{{መዋቅር}}