ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 65፦
[[Image:Evolsex-dia2a.svg|thumb|right|upright=1.1| ወሲብ የፍጡራን ተመራጭ ገፅታ በድቅለት እንዲሰራጭ ይረዳል። የሚታየው ምስል በወሲባዊ ፍጡር ውስጥ የሚገኙ የዘር ምዝግቦችን (allele) የተደጋጋሚነት ዝግምተ ለውጥ የሚያመዛዝን ነው። (a) እና ኢወሲባዊ መንጋ (b). ቋሚው አምድ ድግምጋሚን ሲያሳይ አግዳሚው አምድ የጊዜ ሂደትን ያሳያል። a/A እና b/B የሚባሉት የዘር ምዝግቦች ህላዊነታቸው አቦሰጥ ነው። ተፈላጊው ዘራዊ ገፅታ AB ከ (a) ዳግም ውህደት በኋላ ብፍጥነት ይሰራጫል, ሆኖም ግን ከ(b) ውስጥ ራሱን ችሎ መከስተ አለበት.]]
 
ወሲባዊ እርባታ ለመጀመሪያ ግዜ የተከሰተው ከአንድ ቢሊዮን አመታት በፊት እንደሆነ ይገመታል። የወሲብ ክስተት አሃዳዊ ህዋስነት ካላቸው ዩክሮይት(eukaryotes)ከሚባሉ ደቂቅ ህላውያን የመነጨ ነው። የወሲባዊ እርባታ ክስተት እንዲሁም እስክግዜያችን የመዝለቁ ጉዳይ አከራካሪና እልባት ያተገኘለትያልተገኘለት ጉዳይ ነው። አንዳንድ መጣኝ መላምቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፤ ወሲብ ፅንሶቹ የተለያየ ዘራዊ ባህርይ እንዲኖራቸው ያግዛል፣ ወሲብ ጠቃሚ የዘር ገፅታዎች እንዲሰራጩ ይረዳል፣ ወሲብ የማይጠቅሙ ገፅታዎች እንዳይሰራጩ ይረዳል፣ የሚሉት ይገኙበታል።
 
ወሲባዊ እርባታ ዩክሮይት ብቻ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። ዩክሮይት፣ በውስጣቸው ምዕከላዊማዕከላዊ (nucleus)እና ከባቢ (mitochondria)ያሏቸው ህዋሳት ናቸው። ከእንሰሳት በተጨማሪ፣ ዕፅዋት እና ፈንጋይ እንዲሁም ሌሎች ዩክሮይት (ምሣሌ፣ የወባ ነቀዝ) ወሲባዊ እርባታን ይጠቀማሉ። አንዳንድ ደቂቅ ህላውያን ለምሳሌ ባክቴርያ አካላዊ ውህደትንውህደት (conjugation)የሚባለውን ድቀላ ይጠቀማሉ። ይህ ድቀላ ወሲባዊ ባይሆንም የዘር ምልክቶች እንዲዳቀሉና አዲስ ፅንስ እንዲፈጠር ይረዳል።
 
ወሲባዊ እርባታን ወይንም ወሲባዊ ድቅለትን ያረጋግጣል ተብሎ የሚታመነው ክስተት የጋሜት ልዩነትና የድቀላው አሃዳዊነት ናቸው። በአንድ አይነታዊ ፍጡር የተለያዩ ጋሜት መኖራቸው እንደ ወሲባዊ ድቅለት ቢቆጠርም፣ በህብረ ህዋስ እንሥሣት ውስጥ ሳልሳዊ ጋሜት ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም።