ከ«ዘውዱ ጌታቸው» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[Image:zewdu.jpg|thumb|300px|ዘውዱ ጌታቸው]]'''ዘዉዱ ጌታቸው''' ([[አዲስ አበባ]] [[1952]] -አዲስ አበባ [[ታህሳስታኅሣሥ 18]] ቀን [[1997]] ዓ.ም)፣ [[ኤች.አይ.ቪ]]|[[ኤድስ]]ን በሚመለከት ፀጥታና ዝምታ በሰፈነበት ወቅት ራሱ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖር ይፋ በማዉጣት «ትዉልድ ይዳን በእኛ ይብቃ» ! ብሎ ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን ለመዋጋት የተነሳ [[ኢትዮጵያ]]ዊ ጀግና ነበረ። ዘዉዱ ጌታቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በመስፍን ሀረር ትምህርት ቤት ፤የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ተምሮ ካጠናቀቀ በኋላ በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋክልቲ በመግባት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቱንም አጠናቋል። በአሰላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት እንዲሁም በዚላ፥በበርታ፥በሱርና፥በሶጀት ኮንስትራክሽን ድርጅቶች በመካኒክነት ሠርቷል።
 
«እኔ ከቫይረሱ ጋር የምኖር ነኝ።» በማለት የኢትዮጵያ ሕዝብን በአደባባይ ለማስተማር መዉጣት እጅግ በጣም ጥቂት ቆራጦች ብቻ የሚደፍሩት ተግባር በነበረበት ጊዜ ብቅ ብሎ ለአገር የሚጠቅም ታላቅ ተግባር ሲያከናዉን የቆየ ሰዉ ነበረ። ዘዉዱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ማህበር «[[ተስፋ ጎህ ኢትዮጵያ]]ን» በ1990 ዓ.ም ከአሥር ጓደኞቹ ጋር በመመስረት ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖች መብታቸዉን ለማስከበር እንዲታገሉ ከማሰባሰቡም በላይ ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ ጉልህ አስተዋፅኦ አድርጓል።