ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 99፦
 
===ኢ-ሥነዘራዊ===
[[Image:Ocellaris clownfish.JPG|thumb|upright=1.1|left|ክላውን አሶች[[Clownfish]] ከጅምሩ ተባእት ሲሆኑ ከከባቢ ካሉት ሁሉ በአካሉ አንጋፋ የሆነው ግላዊ የእንስትነትን ፆታ ይይዛል። ]]
 
በሥነዘራዊ የፆታ ውሳኔ የማይጠቀሙ፣ ነገር ግን በከባቢ የተፈጥሮ ፀባዮች የሚመረኮዝ ፆታዊ ውሳኔ ያላቸው በዙ ፍጡራን አሉ። ብዙ ደመ ቀዝቃዛ እንሽላሊት መሰል (reptile)ፍጡራን የከባቢ ሙቀት ላይ የተመረኮዘ የፆታ መወሰኛ ዘዴ ይጠቀማሉ። ፅንሱ በእድገቱ ጊዜ የሚሰማው ከባቢ ሙቀት የሽሉን ፆታ ይወስናል። ላምሳሌ በአንዳንድ የኤሊ አይነቶች ውስጥ ፅንሱ በእርግዝና ጊዜ ከባቢው ቀዝቀዝ ያለ ከሆነ ሽሉ ተባእት ይሆናል። ይህ የፆታ መወሰኛ ሙቀት መጠን ወሰናዊ ልዩነቱ ከ1-2°C አያልፍም።
 
ብዙ የአሳ ዘሮች በህልውናቸው ዘመን ፆታ የመለወጥ ፀባይ ይታይባቸዋል። ይህ ክስተት አሃዳዊ ፍናፍንትነት (sequential hermaphroditism) ይባላል። በአንዳንድ የአሳ አይነቶች በአካሉ አንጋፋ የሆነው ግላዊፍጡር እንስት ሲሆን፣ አናሳ የሆነው ደግሞ ተባእት ይሆናል። በሌሎች የአሳ አይነቶች ለምሳሌ 'wrasses' የዚህ የተገላቢጦሽ ሁኔታ ይታያል፣ ማለትም ግላውያኑ በወጣትነታቸው እንስት ሆነው ያድጉና ሲተልቁ የተባእትነት ፆታ ይይዛሉ። እነዚህ አሃዳዊ ፍናፍንትነትን የሚከተሉት ፍጡራን የሁለቱንም ፆታዎች የዘር ህዋስ ወይንም ጋሜት በህይወት ዘመናቸው ጊዜ ማመንጨት ቢችሉም፣ በአንድ በተወሰን ጊዜ ግን ወይ ሴቶች ናቸው ወይ ወንዶች ናቸው።
 
በአንዳንድ ትላልቅ ዛፎች በተለይ ፈርን (ferns)ተብለው በሚታወቁት ውስጥ መደበኛው ፆታ ፍናፍንትነት ነው፣ ሆኖም በቀደምተነት የፍናፍንትን ተክል ያበቀለ አፈር ላይ የሚያድጉት ግላውያን በሚያገኙዋቸው ፍቅፋቂ ንጥረነገሮች ተፅዕኖ ምክንያት የተባእትነትን ፆታ ይዘው ያድጋሉ።
 
{{መዋቅር}}