ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 90፦
በሥነዘራዊ ፆታ መወሰኛ ዘይቤዎች፣ የአንድ ግላዊ ፆታ የሚወሰነው በሚወርሰው የዘር ምልክት (genome)ነው። የሥንዘራዊ ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በተዘባ ሁኔታ የሚወረስ፣ የክሮሞሶማዊ ውህደት ላይ የተመረኮዘ ነው። እነዚህ ክሮሞሶሞች በውስጣቸው የፆታን ክስተት የሚወስኑ የዘር ምልክቶች ይይዛሉ። የፅንሱ ፆታ የሚወሰነው ባሉት የፆታ ክሮሞሶም አይነቶች ወይንም በሚገኙት ክሮሞሶሞች ብዛት ነው። የሥነዘራዊ ፆታ ውሳኔ በክሮሞሶማዊ ውቅረት ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ፣ አብዛኛውን ግዜ እኩል የተባእትና የእንስት ቁጥር ያላቸውን ፅንሶች ያመነጫል።
 
ሰብአውያንና ሌሎች አጥቢ እንስሳት የ 'XY' የፆታ መወሰኛ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። 'Y' ክሮሞሶም የወንድ ፅንስ እንዲፈጠር የሚያግዙ ማነሳሻ ነገሮችን ይይዛል። የ 'Y' ክሮሞሶም በሌለ ግዜ በመደበኝነት የሚከሰተው ፅንስ ተባእትእንስት ይሆናል። ስለዚህ 'XX' ኣጥቢ እንሥሣት እንስት ሲሆኑ 'XY' የሆኑት ደግሞ ተባዕት ናቸው። የ 'XY' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በሌሎች ፍጡራን ለምሣሌ በዝንቦችና በእፅዋት ውስጥ ይገኛል። አንዳንድ ግዜ፣ ለምሳሌ በዝንቦች ውስጥ የፆታ ወሳኝ የሚሆነው የ 'Y' ሳይሆን የ'X' ክሮሞሶም ነው።
 
አእዋውፍ የ'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ሲኖራቸው ከላይ ከተጠቀሰው የሚፃረር ሁኔታ ይታይባቸዋል። የ'W' ክሮሞሶም የእንስት ፅንስን መከሰት የሚያነሳሱ ነገሮችን ሲይዝ መደበኛው ፆታ ግን ወንድ ነው። በዚህ ሁኔታ ZZ ግላውያን ተባእት ሲሆኑ፣ 'ZW' ደግሞ እንስት ናቸው። ብዙ በራሪዎች፣ ቢራቢሮዎችን ጨምሮ የ'ZW' የፆታ መወሰኛ ዘዴን ይከተላሉ። ባየናቸው የ 'XY' እና 'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤዎች ውስጥ የፆታ መወሰኛው ክሮሞሶም በአካሉ በአብዛኛው አናሳ ሲሆን የፆታ መወስኛና ማነሳሻ ምልክቶችን ከመያዙ በስተቀር ሌሎች ነገሮች በውስጡ በብዛት አይኖሩም።