ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 88፦
 
===ሥነ ዘራዊ (Genetic)===
በሥነዘራዊ ፆታ መወሰኛ ዘይቤዎች፣ የአንድ ግላዊ ፆታ የሚወሰነው በሚወርሰው የዘር ምልክት (genome)ነው። የሥንዘራዊ ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በተዘባ ሁኔታ የሚወረስ፣ የክሮሞሶማዊ ውህደት ላይ የተመረኮዘ ነው። እነዚህ ክሮሞሶሞች በውስጣቸው የእድገትንየፆታን ሂደትክስተት የሚወስኑ የዘር ምልክቶች ይይዛሉ። የፅንሱ ፆታ የሚወሰነው ባሉት የፆታ ክሮሞሶም አይነቶች ወይንም በሚገኙት ክሮሞሶሞች ብዛት የሚወሰን ይሆናል።ነው። የሥነዘራዊ ፆታ ውሳኔ በክሮሞሶማዊ ውቅረት ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ፣ አብዛኛውን ግዜ እኩል የተባእትና የእንስት ቁጥር ያላቸውን ፅንሶች ያመነጫል።
 
ሰብአውያንና ሌሎች አጥቢ እንስሳት የ 'XY' የፆታ መወሰናመወሰኛ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። 'Y' ክሮሞሶም የወንድ ፅንስ እንዲፈጠር የሚያግዙ ማነሳሻ ነገሮችን ይይዛል። የ 'Y' ክሮሞሶም በሌለ ግዜ በመደበኝነት የሚከሰተው ፅንስ ተባእት ይሆናል። ስለዚህ 'XX' ኣጥቢ እንሥሣት እንስት ሲሆኑ 'XY' የሆኑት ደግሞ ተባዕት ናቸው። የ 'XY' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በሌሎች ፍጡራን ለምሣሌ በዝንቦችና በእፅዋት ውስጥ ይገኛል። አንዳንድ ግዜ፣ ለምሳሌ በዝንቦች ውስጥ የፆታ ወሳኝ የሚሆነው የ 'Y' ሳይሆነሳይሆን 'X' ክሮሞሶም ነው።
 
አእዋውፍ 'ZW ' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ሲኖራቸው ከላይ ከተጠቀሰው ተፃራሪየሚፃረር ሁኔታ ይታይባቸዋል። 'W' ክሮሞሶም የእንስት ፅንስን መከሰት የሚያነሳሱ ነገሮችን ሲይዝ መደበኛው ፆታ ግን ወንድ ነው። በዚህ ሁኔታ ZZ ግላውያን ተባእት ሲሆኑ፣ 'ZW' ደግሞ እንስት ናቸው። ብዙ ተባራሪዎች፣በራሪዎች፣ ቢራቢሮዎችቢራቢሮዎችን ጨምሮ 'ZW' የፆታ መወሰኛ ዘዴን ይከተላሉ። ባየናቸው የ 'XY' እና 'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤዎች ውስጥ የፆታ መወሰኛው ክሮሞሶም በአካሉ በአብዛኛው አናሳ ሲሆን የፆታ መወስኛና ማነሳሻ ምልክቶችን ከመያዙ በስተቀር ሌሎች ነገሮች በውስጡ በብዛት አይኖሩም።
 
ብዙ ነፍሳት የሚከተሉት የፆታ መወሰኛ ዘይቤ ባሉት የክሮሞሶም ብዛት ላይ የተመረኮዘ ነው። ይህ XX/XO ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ይባላል። 'O' የፆታ መወሰኛ ክሮሞሶም አለመኖርን ያመላክታል። በነኝህ ፍጡራን ውስጥ ያሉት ክሮሞሶም ዳይፕሎይድ ሲሆኑ፣ ሆኖም ግን አንዳንዶቹ አንድ ወይንም ሁለት 'X' ክሮሞሶም ሊወርሱ ይችላሉ። በፌንጣዎች ለምሳሌ አንድ 'X' ክሮሞሶም የሚወርሰው ፅንስ ወንድ ሲሆን፣ ሁለቱን የሚወርሰው ደግሞ ሴት ይሆናል። nematode C. elegans በሚባሉት ትሎች ውስጥ አብዛኞቹ ራስ በራስ ተዳቃዮች 'XX' ፍናፍንቶች ሲሆኑ አልፎ ደግሞ በክሮሞሶም ውርሰት ውዝግብ ምክንያት 'X' ክሮሞሶም ብቻ ያላቸው ግላውያን ሊፈጠሩ ይችላሉ። እነኝህ 'XO' ግላውያን ተራቢ ተባእት ይሆናሉ። (ከሚፀንሷቸው ፅንስ ግማሾቹ ተባእት ይሆናሉ።)