ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 94፦
አእዋውፍ የ 'ZW ' ፆታ መወሰኛ ሲኖራቸው ከላይ ከተጠቀሰው ተፃራሪ ሁኔታ ይታይባቸዋል። 'W' ክሮሞሶም የእንስት ፅንስን መከሰት የሚያነሳሱ ነገሮችን ሲይዝ መደበኛው ፆታ ግን ወንድ ነው። በዚህ ሁኔታ ZZ ግላውያን ተባእት ሲሆኑ፣ 'ZW' ደግሞ እንስት ናቸው። ብዙ ተባራሪዎች፣ ቢራቢሮዎች የ 'ZW' የፆታ መወሰኛ ዘዴን ይከተላሉ። ባየናቸው የ 'XY' እና 'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤዎች ውስጥ የፆታ መወሰኛው ክሮሞሶም በአካሉ በአብዛኛው አናሳ ሲሆን የፆታ መወስኛና ማነሳሻ ምልክቶችን ከመያዙ በስተቀር ሌሎች ነገሮች በውስጡ በብዛት አይኖሩም።
 
ብዙ ነፍሳት የሚከተሉት የፆታ መወሰኛ ዘይቤ ባሉት የክሮሞሶም ብዛት ላይ የተመረኮዘ ነው። ይህ XX/XO ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ይባላል። 'O' የፆታ መወሰኛ ክሮሞሶም አለመኖርን ያመላክታል። በነኝህ ፍጡራን ውስጥ ያሉት ክሮሞሶም ዳይፕሎይድ ሲሆኑ፣ ሆኖም ግን አንዳንዶቹ አንድ ወይንም ሁለት 'X' ክሮሞሶም ሊወርሱ ይችላሉ። በፌንጣዎች ለምሳሌ አንድ 'X' ክሮሞሶም የሚወርሰው ፅንስ ወንድ ሲሆን፣ ሁለቱን የሚወርሰው ደግሞ ሴት ይሆናል። nematode C. elegans በሚባሉት ትሎች ውስጥ አብዛኞቹ ራስ በራስ ተዳቃዮች 'XX' ፍናፍንቶች ሲሆኑ አልፎ ደግሞ በክሮሞሶም ውርሰት ውዝግብ ምክንያት 'X' ክሮሞሶም ብቻ ያላቸው ግላውያን ሊፈጠሩ ይችላሉ። እነኝህ 'XO' ግላውያን ተራቢ ተባእት ይሆናሉ። (ከሚፀንሷቸው ፅንስ ግማሾቹ ተባእት ይሆናሉ።)
 
ሌሎች ነፍሳት፣ ለምሳሌ ንቦችና ጉንዳኖች haplodiploid የሚባለውን የፆታ መወሰና ዘይቤ ይጠቀማሉ። በዚህ ጊዜ ዳይፕሎይድ የሆኑት ግላውያን በአብዛኛው እንስት ሲሆኑ፣ ሃፕሎይድ ይሆኑት (ከተደቀለ እንቁላል የሚያድጉት) ደግሞ ተባእት ናቸው። ይህ የፆታ መወሰኛ ዘይቤ፣ በቁጥር ረገድ ወዳንዱ ፆታ ዝንባሌ ላለው የፆታ ስርጭት ይዳርጋል። የህ የሚሆንበት ምክንያት የፅንሱ ፆታ የሚወሰነው በድቅለት ጊዜ እንጂ በሚዮሲስ ጊዜ በሚከሰተው ክሮሞሶማዊ ይዘት አለመሆኑ ነው።
 
{{መዋቅር}}