ከ«ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[Image:Kidane Aba Kesto.jpg|thumb|300px|ደጃ/ኪዳኔ በአርበኝነት]]
 
'''ኪዳኔ ወልደመድኅን''' ዓርብ ሌሊት [[ሐምሌ 2|ሐምሌ ፪]] ቀን [[፲፱፻፯]] ዓ.ም [[ቡልጋ]] በ[[ከሰም ]]ወረዳ፤ [[የለጥ]] ቀበሌ፤ ልዩ ስሙ ቡሄ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ ከናታቸው ከወይዘሮ አስካለ ደጀን እና ከአባታቸው ከቀኛዝማች ወልደመድኅን አዩደረስ ተወልደው [[ነሐሴ 10]] ቀን በጥምቀት ስም ኪዳነ ማርያም ተሰይመው [[የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ]][[ ቤተ ክርስቲያን]] [[ክርስትና]] ተነሱ። አባታችው ቀኛዝማች ወልደመድኅን ትውልድ ሃገራቸው ወበሪ ሲሆን፤ በዘመኑ የታወቁ ስመጥሩ ጠበቃ ነበሩ። ከወይዘሮ አስካለም ጋር የተገናኙት ሁለቱም እወረዳው ፍርድ ቤት [[ኮረማሽ]] ለየጉዳያቸው ሄደው እንደነበር ይነገራል። ኪዳነማርያምም እስከ ፲፪ ዓመት እድሜያቸው እዚያው ቡሄ አምባ ከአያታቸው አቶ ደጀን ደብሩ ቤት እንዳደጉና የቄስ ትምህርት ቤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደተከታተሉ ተጽፏል። ከዚህ በኋላ አባታቸው ቤት እያደጉ የ[[አማርኛ]]ና የ[[ግእዝ]] ትምህርት አጠናቀዋል።
 
አካለ መጠን ሲደርሱ በ፲፰ዓመታቸው በ[[፲፱፻፳፭]] ዓ.ም. [[አዲስ አበባ]] በ[[ክብር ዘበኛ]] ደንብ ተቀጥረው ወዲያው በ[[ቀኅሥ|ንጉሠ ነገሥቱ]] ትዕዛዝ ከ69 አዲስ ወታደሮች ጋር [[ባሌ]] ተመድበው እስከ [[፲፱፻፳፯]] ዓ.ም ድረስ በተራ ወታደርነት ከዚያም በ ሃምሳ ዓለቃና በባሻነት ማእረግ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ [[ጣሊያን]] [[ኢትዮጵያ]]ን ሊወር ሲመጣ በ[[፲፱፻፳፰]] ዓ.ም በምስራቅ ደቡብ በ[[ደጃዝማች በየነ መርዕድ]] እና በ[[ጄነራል አስፋው ወልደ ጊዮርጊስ]] መሪነት፤ የመጀመሪያ ልጃቸው ዓለማየሁ በተወለደ በዘጠኝ ቀኑ፤ [[ጥቅምት ፲፩]] ቀን [[፲፱፻፳፰]] ዓ.ም ከጎባ ወደ [[ኦጋዴን]] ዘመቱ።
መስመር፡ 27፦
ከፋ ውስጥ እንደተሾሙ (፲፱፻፵፫ ዓ.ም) ከጠቅላይ ገዢው ጋር ባለመስማማታቸው ተሽረው ንጉሠ ነገሥቱ ከስልጣን እስከወረዱ ድረስ በእስራትና በግዞት ሃያ ሦስት ዓመት ሙሉ ለሃገሩ እንዳልተጋደለ፣ በአርበኝነት ደሙን እንዳላፈሰሰ፣ ለኢትዮጵያ ነጻነት መስዋዕት እንዳልሆነ ተቆጥረው፣ ንጉሠ ነገሥቱ ለቅርብ ሎሌአቸው አድልተው ደጃዝማች ኪዳኔን ከሀገር አገልግሎት አስወገዷቸው።
 
ንጉሠ ነገሥቱ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ደጃዝማች ኪዳኔ በመላ [[የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር|ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር]] ሊቀመንበርነት ተመርጠው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ሃገራቸውንንና [[የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞት ማህበርንማህበር]]ን ወክለው ሮም[[ሮማ]] ላይ በተካኼደው የዓለም አቀፍ ጸረ ኑክሊየር መሣሪያ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሲጓዙ [[መስኮብ]] (Moscow) ላይ [[ጥቅምት 9|ጥቅምት ፱]] ቀን [[፲፱፻፸፪]] ዓ.ም. በተወለዱ በስልሳ ዓምስትአምስት ዓመታቸው አረፉ። ቀብራቸውም [[መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን]] [[ጥቅምት ፲፭ቀን15|ጥቅምት ፲፭]] ቀን ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ተከናውኗል።
 
[[Image:Dejazmachkidane.jpg|thumb|550px|ደጃ/ኪዳኔ ወልደመድኅን የኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ሊቀ መንበር|centre]]