ከ«ክሻትሪያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
robot Adding: en:Kshatriya; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[Fileስዕል:Mahvra.jpg|thumb|200px|የ[[ጃይን]] ሃይማኖት አስተማሪ [[ማሃዊራ]] (607-535 ዓክልበ.) የክሻትርያ መደብ አባል ነበረ።]]
'''ክሻትሪያ''' የ[[ሕንድ|ህንዳውያን]] ኅብረተሠብ በተለያዩ 4 መደባት የሚከፋፈልበት አንዱ የህብረተሰባዊ ክፍል (''ካስት'') ነው። በዚህ አከፋፈል ዘዴ የወታደሮችና የገዢዎች ክፍል እሱ ነው። ክሻትሪያ ከ[[ብራህሚን]] (ቄሳውንትና አስተማሮች) በታችና ከ[[ቫይስያ]] (ነጋዴዎች) እንዲሁም ከ[[ሹድራ]] (ሠራተኞች፣ አገልጋዮች) በላይ ሆኖ ይቆጠራል።
 
በመጀመርያ በጥንት ይህ ደረጃ በሰው ችሎታ፣ ተግባርና ጸባይ ምክንያት ሊገኝ የቻላ ሲሆን፣ በዘመናት ላይ ግን የተወረሰ ማዕረግ (በዘር የሚዛወር) ብቻ ሆነ። በአንዳንድ ወቅት ደግሞ የክሻትሪያ (መኳንንት) ክፍል ከብራህሚኖች (ቄሳውንት) ክፍል ይልቅ ላየኛነቱን ይይዝ ነበር። ብራህሚኖችም በኋላ የበለጡት ከትግል በኋላ እንደ ሆነ ይታመናል።
 
የቃሉ ሥር በ[[ሕንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ]] «*ክሺ» 'መግዛት' ሲሆን ለዚሁ ብዙ የተዛመዱ ቃሎች (እንደ [[ሳንስክሪት]] «ክሻትራ» 'ግዛት') ይኖራሉ። በ[[ጥንታዊ ፋርስኛ]] በኩል «ሕሻጥራ» ማለት 'ሃይል፣ መንግሥት' ነበረ፤ የ«ሕሻያጢያ» ትርጉም የፋርስ ንጉሠ ነገስት ሆኖ ከዚህ በዘመናዊ [[ፋርስኛ]] ንጉሥ [[ሻህ]] ይባላል። በአማርኛ፣ [[ቼዝ]] (ሰንጠረዥ) የሚባል ጨዋታ ስም ከዚህ የመጣ ነው። በተጨማሪ በፋርስ ታሪክ የጠቅላይ ግዛት ወይም አገረ ገዥ ማዕረግ «ሕሻጥራ-ፓዋ» (የግዛት ጠባቂ) በኋላ «[[ሳትራፕ]]» ሆነ። ሌሎች ቃላት በ[[ታይላንድኛ]] «ካሳት» 'ንጉስ' በ[[መላይኛ]]ም «ሳትሪያ» 'ጀግና' ከ«ክሻትሪያ» የተነሡ ናቸው።
 
በ[[ሕንዱ ሃይማኖት]] መጻሕፍት የክሻትሪያ ታሪክና ሚና ይወሰናል። በ''[[ርግ ዌዳ]]'' ዘንድ እያንዳንዱ መደብ ወይም 'ዋርና' ከፈጣሪ አምላክ (ብራህማ) ሰውነት ተነሥቶ የክሻትሪያ መደብ የተነሣ ከትከሾቹና ከክንዶቹ ነበረ። በሌላ ትርጉም ከጥፋት ውሃ ያመለጠው ሕግ ሰጪ [[ማኑ]] የ[[አርያ]]ን ኅብረተሰብ ባከፋፈለበት ጊዜ ክሻትርያዎቹ ማርሻል አርትስ (እንደ [[ጁዶ]]፣ [[ካራቴ]] ወዘተርፈ) የተማሩት ነበሩ። እያንዳንዱ ዋርና (ካስት) በልዩ ቀለም ሲመለከት የክሻትሪያ ቀለም ቀይ ሆነ።
 
በሌሎች መጻሕፍት መሠረት፣ በዙሪያ የተገኙ ሕዝቦች በድሮ እንደ ክሻትርያ ቢቆጠሩም፣ የብራህሚኖችን ሃይማኖት ግን በደንብ ስላልጠበቁ፣ በኋላ ከክሻትርያው ሁኔታ ወደቁ። ከነዚህም፣ ሳካዎቹ (የ[[እስኩቴስ]] ሰዎች)፣ ያዋኖቹ (የ[[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] ሰዎች)፣ ፓህላቮቹ (የ[[ፋርስ]] ሰዎች)፣ ድራዊዶቹ (የደቡብ ሕንድ ጥቁሮች) እና የ[[ቻይና]] ሰዎች ሁላቸው በቀድሞ ክሻትሪያዎች ነበሩ። ዛሬ ግን አብዛኞቹ ክሻትርያዎች በህንድ አገር የአርያኖች (ነጮች) ሕዝብ አባላት ናቸው። ከሕንድ አገር ውጭ ከክሻትርያ የተወለዱ ዘሮች በተለይ በ[[ኢንዶኔዥያ]]፣ በ[[ቬትናም]]ና በ[[ሽሪ ላንካ]] ይገኛሉ። የዛሬው ክሻትርያ ቤተሠቦች በጠቅላላው ከመደባቸው ውጭ አይጋቡም።
 
ከሕንድ አገር ስርወ ነገስታት በቀር፣ በታሪክ ውስጥ ሌሎች የተገነኑ ክሻትርያዎች የ[[ቡድሃ ሃይማኖት]] አስተማሪ [[ጎታማ ቡድሃ]] እና የ[[ጃይን ሃይማኖት]] አስተማሪ [[ማሃዊራ]] ናቸው። በቡድሂስትና በጃይን ሃይማኖቶች ግን የ'ክሻትርያ' ትርጉም «ጦረኛ» ሳይሆን «ገበሬ»፣ «ባለመሬት» ብቻ ነው። በህንድ ሃይማኖት በኩል፣ ዋና አማልክታቸው [[ራማ]] እና [[ክሪሽና]] ክሻትርያዎች ይባላሉ።
 
[[መደብ:ታሪክ]]
መስመር፡ 16፦
 
[[de:Kshatriya]]
[[en:Kshatriya]]
[[es:Chatria]]
[[fr:Kshatriya]]
[[gu:ક્ષત્રિય]]
[[ko:크샤트리아]]
[[hi:क्षत्रिय]]
[[id:Kesatria]]
[[ja:クシャトリヤ]]
[[ko:크샤트리아]]
[[mr:क्षत्रिय]]
[[nl:Kshattriya]]
[[ja:クシャトリヤ]]
[[pl:Kszatrija]]
[[pt:Xátria]]