ከ«ሦስቱ እኅትማማች» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''«ሦስቱ እኅትማማች»''' በእርሻ ተግባርስሜን አሜሪካ ኗሪዎች የተለማና የሚጠቀም የግብርና ዘ…»
(No difference)

እትም በ14:05, 30 ማርች 2009

«ሦስቱ እኅትማማች»እርሻ ተግባርስሜን አሜሪካ ኗሪዎች የተለማና የሚጠቀም የግብርና ዘዴ ነው። ሦስቱ ዋና ዋናዎች አዝመራዎቻቸው እነሱም በቆሎባቄላ፣ እና ዱባ (ወይም ቦሎቄ) አንድላይ ሲተከሉ ማለት ነው።

በዚሁ ዘዴ አስቀድሞ ብዙ ትንንሽ የአፈር ቁልል ይደረጋል። የእያንዳንዱ ቁልል ከፍታ 30 ሴንቲ ሜትር ሲሆን ስፋቱ 50 ሴንቲ ሜትር ይሆናል። በመሃሉ አያሌ የበቆሎ ዘር አንድላይ ይጨመራል። በአንዳንድ ጎሣ ልማድ፣ ማዳበሪያ እንዲሆን የበሰበሰ ዓሣ ከዘሩ ጋር ይቀበራል።

የበቆሎው ቁመት እስከ 15 ሴንቲ ሜትር ድረስ ሲወጣ፣ ባቄላውና ዱባው በመፈራረቅ እንዲከብቡት ይዘራሉ።

እነዚህ ሦስት ሰብሎች በመጠቃቀም ይባበራሉ። በቆሎው ለባቄላው መንጠላጠል የሚችል መዋቅር ስለሚሰጥ፣ ምሰሶ ማቆም አያስፈልግም። ባቄላውም ለሌሎቹ አትክልት በጣም አስፈላጊ የሆነውን ናይትሮጀን ወደ መሬት ለመጨመር ልዩ ችሎታ አለው። ዱባውስ በመሬት ገጽ ላይ እጅግ ሲስፋፋ፣ መዓልቱን በመሸፈኑ አረምን ይከለክል፤ እንዲሁም ሀረጉ ትንሽ እሾህ የመሰለውን ጽጉር ስላለው የሚጎዱ ነፍሳት ይከለክላል፤ ከዚህም በላይ የዱባ ቅጠል እርጥበት በመጠበቁ እንደ ማደበሪያ ያገልግላል።

ሦስቱ ተክሎች ስለዚህ በጣም የሚስማሙ በመሆናቸው የበለጠ መልካም ምርት ሊያስገኙ ይቻላል። ይህ ዘዴ በሰፊ እርሻ ወይም ገነት ላይ ሲጠቀም ሚልፓ ይባላል።


የውጭ መያያዣዎች