ከ«ላሊበላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
link mar
መስመር፡ 19፦
የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እንደተሰሩ የሚታመን ሲሆን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ፀሃፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ [[ቴምፕላርስ]] የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል። እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተክርስቲያኖች አሉ።
 
ንጉሡ ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘው፣ ሲወለድ በንቦች ስለተከበበ ነው ይባላል። ላል ማለት [[ማር]] ማለት ሲሆን፤ ላሊበላ ማለትም -ላል ይበላል (ማር ይበላል) ማለት አንደሆነ ይነግራል። ውቅር ቤተክርስቲያናቱን ንጉሡ ጠርቦ የስራቸው ከመላእክት እገዛ ጋር እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይነግራል። በ16ኛው ከፍለ ዘመን አውሮፓዊ ተጓዥ ላሊበላን ተመልክቶ "ያየሁትን ብናግር ማንም እንደኔ ካላየ በፍጹም አያምነኝም" ሲል ተናግሮ ነበር።
 
በላሊበላ 11 ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ (ባለ መስቀል ቅርፁ) ሲታይ ውሃልኩን የጠበቀ ይመስላል። ቤተ መድሃኔ ዓለም የተባለው ደግሞ ከሁሉም ትልቁ ነው።