ከ«ውክፔዲያ ውይይት:የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 11፦
 
--ሀሁ
----
ጤና ይስጥልኝ
 
# 'December' የእንግሊዝኛ ወር ስም ስለሆነ በላቲን ዓልፋቤት ቢጻፍ ስኅተት አይመስለኝም። ይሁንና ብዙ ጊዜ ቃሉ በፊደል እንደ 'ዲሤምበር' በሚመሥል አጻጻፍ ታይቷል። የወሮች ስም በሌሎቹ ቋንቋዎች ሌላ አጠራር እንዳላቸው ይታወሳል - በፈረንሳይኛ Décembre ዴሳም ይሰማል፣ በእስፓንኛም Diciembre ዲስየምብሬ ይባላል። የውጭ አገር ቃላት በላቲን አልፋቤት ሲሆኑ አንዳንዴ ቀጥታ በፊደል መካከል እንደዚያ መታየታቸው የተለመደ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ አጠራሩ እርግጥ ቢታወቅ ወደ ፊደል መልክ ተለውጠው ተገኝተዋል። ስለዚህ ሁለቱ ዘዴዎች ተቀባይነት አላቸው።
#: ለመሆኑ በዚህ ጠቅላላ ፕሮጀክት interface ላይ የጎርጎርዮስ ወሮች ሁሉም ቦታ (ለምሳሌ በ'ቅርብ ለውጦች' ላይ) ወደ ኢትዮጵያ ወሮች መቀየር ባይቻለኝም (ቀኖች በቁጥር ስለሚለያዩ) የእንግሊዝኛ ወር ስም ግን ወደ ፊደል (እንደ 'ዲሴምበር') በቀላል መቀየር እችላለሁ። ይህ ዘዴ በ[[wikt:|አማርኛ ውክሽኔሪ]] አሁን በከፊል ይጠቀማል እዚህም ሊደረግ ይቻላል ምን ታስባላችሁ?
# መጣጥፍ ውስጥ፣ ወይም የግዕዝ ወይም የአማርኛ ብዙ ቁጥር አይነት ይፈቀዳል። ሁለቱ ትክክለኛ ናቸው። ሁለቱ በአንዱ ቃል ላይ (ለምሳሌ፣ 'ቃላቶች') ግን ከቶ አይገባም! በአርዕስት ግን፣ ከተቻለ ነጠላ ቁጥር ይመረጣል።
# በኔ አስተያየት ሰረዝ (፣) ከኮማ ለአማርኛ አርዕስት በጣም ይሻላል። ይህ ክፍል በእልፍአለም (ሌላው ሳይሶፕ) ስለ ተጻፍ ግን ጥልቅ ማለት አልወደድኩም! እሱን ጠይቀን ምናልባት ልናሻሽለው ብንችል እናያለን...!
 
በጠቅላላ በማንኛውም ገጽ ላይ እዚህ ሳይቀር ማዘጋጀትና ማረም ለሰው ሁሉ ይፈቀዳል!
 
ይህ ሁሉ የኔ እይታ ነው፤ የኔ ውልደት ቋንቋ ነው ለማለት ስለማልችል ግን እንዴት እንደሚመስሎ ማወቅ እወዳለሁ!
ከክብር ጋር፣ --[[User:Codex_Sinaiticus|ፈቃደ]] ([[User talk:Codex_Sinaiticus|ውይይት]]) 01:13, 3 June 2006 (UTC)
Return to the project page "የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ".