ዞብል መቃብር የፈረሱ ዞብል መቃብር ነው። ከፋሲል መዋኛ አጠገብ በስተምስራቅ ይገኛል። ዞብል በአንዳንዶች ዘንድ ተወዳጁ የአጼ ፋሲለደስ ፈረስ መሆኑ ሲታመን አልፎ አልፎ ሌሎች ሰዎች ፈረሱ የፋሲለደስ ልጅ የቀዳማዊ ዮሐንስ ፈረስ ነው ይላሉ። ሆነም ቀረም የዞብል መቃብር በክብ ቅርጽ በቅምብብ የተሰራ መታሰቢያ ሲሆን ከቆይታ ብዛት ጉዳት እየደረሰበትና ዛፎች በመካከሉ እየበቀሉበት እየፈረሰ ያለ ምናልባት ብቸኛው የኢትዮጵያ ፈረስ መዘክር ነው።

የዞብል መቃብር
የዞብል መቃብር በ1894[1]
የዞብል መቃብር is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
የዞብል መቃብር

12°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°38′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ Percy Horace Gordon Powell Cotton፣ A sporting trip through Abyssinia a narrative of a nine month' journey from the plains of the Hawash to the snows of Simien፣ 1902